የክርስቲያን አገልግሎት

155/246

ሠራተኞችን መገሰጽ

መከር የመሰብሰብ ልዩ ዘመቻ ላይ ለአገልግሎት የምትወጡ ወገኖች በትጋት የተሞላ ጥረት አድርጉ፤ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ስር ተመላለሱ ለማለት እወዳለሁ፡፡ በክርስትና ተሞክሮቻችሁ ላይ ዕለት ዕለት አዳዲስ ነገሮችን አክሉባቸው፡፡ የተለየ ስጦታ ያላቸው ወገኖች በከፍታም ሆነ በዝቅታ ሕይወት ለሚገኙ አማኝ ያልሆኑ ነፍሳት ይሥሩ፡፡ እየጠፉ ያሉትን ነፍሳት በትጋት ፈልጉ፡፡ ክርስቶስ ዳግም ወደ መንጋው ሊያመጣቸው ስለሚገባ ብርቱ መናፈቅ ስላላቸው የጠፉ ነፍሳት አስቡ! ስለ እውነት የምትነግሯቸውን ነፍሳት ከማሰስ ወደ ኋላ ትበሉ፡፡ በፍርድ ወቅት አንድም ነፍስ “ለምን ስለዚህ እውነት አልነገርከኝም? ስለ እኔ ግድ ያልነበረv ለምንድን ነው?” ብሎ እንዳይጦiዎ--ለአጥቢያ ቤተ ክርስቲያንዎም ሆነ ለጎረቤትዎ የሚሰጡት የወንጌል አገልግሎት ብርሐን በግልጽ የሚያበራና ተስፋ የሚፈነጥቅ ይሁን፡፡ ከእምነታችን ውጪ ለሚገኙ ነፍሳት በጥንቃቄ የተዘጋጁትን የኅትመት ውጤቶች በትጋት የማሰራጨት ሥራ እንሥራ፡፡ አማኝ ያልሆኑ ሕዝቦችን ትኩረት ለመሳብ የሚያስችለንን እያንዳንዱን ዕድል በጥበብ እንጠቀምበት፡፡ ለመቀበል ፈቃደኛ ሆኖ በተዘረጋው እጅ ላይ የኅትመት ውጤቶቻችንን እናኑር፡፡ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጎዳናውንም አስተካክሉ” ለሚለው የመልእክቱ እወጃ ራሳችንን ቀድሰን AT::--MS., “Consecrated Efforts to Reach Unbelievers,” June 5, 1914. ChSAmh 233.1