የክርስቲያን አገልግሎት

153/246

ምዕራፍ 15—መከሩን መሰብሰብ

ግራ አጋቢው ችግር

ጌታ በቸርነቱ ከፊታችን እየቀደመ የሚከፍተውን የወንጌል በር የሚደግፍ በቂ ገንዘብ ማሰባሰብ የምንችለው እንዴት ነው? የሚለው ግራ አጋቢ ጥያቄ ለዓመታት ከፊታችን እየተንገዋለለ ኖሮአል፡፡ የወንጌልን እንቅስቃሴ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ለመተግበር አስፈላጊ የሆኑ ትእዛዛት በአምላካዊው ቃል ላይ በግልጽ ሰፍረው እናነባለን፡፡ የመለኮትን ጣልቃ ገብነት የሚያሳዩ አዎንታዊ አመላካቾችና ፍንጮች መሠራት የሚኖርበትን ሥራ በፍጥነት እንድንከውን በአንድነት ይገፋፉናል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 114. ChSAmh 230.1