የክርስቲያን አገልግሎት

150/246

ልንከተለው የሚገባ ብልህ አካሄድ

አስገዳጁን የእሑድ ሕግ መቃወም ሕጉ እንዲወጣ የሚመኙትን ኃይማኖታዊ ቅንአት ያላቸውን አሳዳጆች ከማጠናከር ውጪ የሚፈይደው አይኖርም፡፡ ሕግ ተላላፊዎች ብለው እንዲጠሩአችሁ ዕድል ሊሰጣቸው የሚችል አንዳችም ቀዳዳ አትተውላቸው፡፡ እግዚአብሔርንም ሆነ ሰውን የማይፈሩ እነዚህ ሰዎች ሰብዓዊውን ፍጡር በማንኛውም ነገር እንዲቆጣጠሩና እንዲመሩ ያለ ልጓም የሚተዉ ከሆነ ብዙም ሳይቆዩ በእንዲv ዓይነቱ አዲስና ያልተለመደ ፍላጎታቸው ትርጉም ስለሚያጡበት እሑድን በአምልኮ ቀን መውሰድ ዘላቂ ወይም ምቹ ሆኖ አያገኙትንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስዎን በእጆ ይዘው በወንጌል ሥራ ወደ ፊት መገስገስዎን ሲቀጥሉ፤ ጠላት የሚገኝበትን ሁኔታ ይበልጥ እንዲባባስ ማድረጉን ይመለከታል፡፡ አንድ ሰው ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለውን ሥራ እየሠራ ትእዛዛቱን ከሚጥስ ተግባር ታቅቦ ከአምላካዊው ፈቃድ ጋር በሰላም የመመላለስን ጥበብ ከተገነዘበ የአውሬውን ምልክት አይቀበልም፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 232. ChSAmh 225.3

እሑድን ለወንጌል ሥራ ስናውል ጅራፉ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን ለማዋረድ እጅግ ደስተኞች ከሆኑ አላግባብ ከሚንቀሳቀሱ ቀናኢያን እጅ ይወሰዳል፡፡ በዚህ ዕለት ወገኖችን በመጎብኘትም ሆነ አምላካዊውን ቃል በማካፈል አገልግሎት ተጠምደን ሲመለከቱን የእሑድን አስገዳጅ ሕግ በማውጣት ሥራችንን ማደናቀፍ ጥቅም _ እንደሌለው ይገነዘባሉ፡፡ Testimonies, vol. 9, pp. 232,233. ChSAmh 226.1

እሑድ ቀን የጌታን ሥራ ወደፊት በማስኬዱ ረገድ አያሌ ጠቀሜታ ያላቸውን ተግባራት ለማከናወን ጥቅም ላይ መዋል ይችላል፡፡ በዚህ ቀን ከቤት ውጪም ሆነ በቤት ውስጥ ስብሰባዎችን ማካሄድ ይቻላል፡፡ የቤት ለቤት አገልግሎት መስጠት ይቻላል፡፡ ጸሐፊዎች ይህን ቀን ለጽሑፍ አገልግሎት ማዋል ይችላሉ፡፡ ሁናቴዎች አመቺ በሆኑ ቁጥር ኃይማኖታዊ አገልግሎቶች በእሑድ ቀን ይካሄዱ፡፡ ስብሰባዎቹ ጣዕም ያላቸውና በጉጉት የሚጠበቁ ይሁኑ፡፡ በልብ ውስጥ መነቃቃት የሚፈጥሩ መዝሙሮች ይዘመሩ፡፡ የአዳኙን ፍቅር የሚያረጋግጡ ቃላት በኃይል ይቅረቡ፡፡ መሻትን በመግዛትና በእውነተኛ ኃይማኖታዊ ተሞክሮ ዙሪያ መልእክቶች ይቅረቡ፡፡ --Testimonies, vol. 9, p. 233. ChSAmh 226.2

በየትምህርት ቤቶቻችን ያሉ መምህራን ይህን ቀን የወንጌላዊ ጥረት አገልግሎት ይስጡበት፡፡ ይህን በማድረጋቸው የጠላትን ዓላማ ማሸነፍ እንደሚችሉ ተገልጾአል፡፡ መምህራን እውነትን የማያውቁ ተማሪዎቻችውን ስብሰባዎች ወደ ሚያካሄዱሁባቸው ስፍራዎች ይውሰዱአቸው፡፡ ይህን አካሄድ በመጠቀም ከማንኛውም ሌላ መንገድ የላቀ ፍሬ ማፍራት ይችላሉ፡ ፡-Testimonies, vol. 9, p. 233. ChSAmh 226.3