የክርስቲያን አገልግሎት

6/246

አምላካዊው በረከትና የብርሃን መተላለፊያ መስመሮች

ሰማያዊ ህይወት ከእኛ ወደ ሌሎች እንዲፈስ የተቀደሰ መተላፊያ መስመር መሆን ይጠበቅብናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ልቦችን በማንጻትና በማጠንከር በመላው ቤተ ክርስቲያን የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖር ያደርጋል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 20. ChSAmh 22.1

እያንዳንዱ የየሱስ ተከታይ በቤተሰቡ _ መሃል፣ በጎረቤቶቹ አካባቢና በሚኖርበት ከተማ ለክርስቶስ የሚሠራው ሥራ አለው፡፡ ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ሁሉ የብርሃን ማስተላለፊያ መስመሮች በመሆናቸው የብርሃንን እውነት ወደ ሌሎች የሚያስተላልፍባቸው የጽድቅ መሣሪያዎቹ ያደርጋቸዋል፡፡ --Testimonies, vol. 2, p. 632. ChSAmh 22.2

የሱስ በውሃ ጉድጓዱ አጠገብ ደክሞትና ርቦት ተቀምጦ በነበረበት ወቅት የተስተዋለው የሥራው ውጤት ለብዙዎች በረከት ያስገኘ ነበር፡፡ እርዳታውን ለመለገስ ፍላጎቱን ያሳያት ያቺ አንድ ነፍስ ወደ ሌሎች መድረሻ ምክንያት በመሆን ብዙዎችን ወደ አዳኙ ይዛ መጣች፡፡ ይህ አካሄድ የእግዚአብሔር ሥራ ሁልጊዜም በምድር ቀስ በቀስ እያደገ እንዲሄድ አስችሎአል፡፡ የእርስዎ ብርሃን እንዲበራ ሲፈቅዱ የሌሎች ይቀጣጠላል፡፡ Gospel Workers, p. 195. ChSAmh 23.1

ብዙዎች ለተሰጣቸው ብርሃንና ተሞክሮ ኃላፊነታቸው በተለይ ለክርስቶስ ብቻ እንጂ በምድር ላሉ ተከታዮቹ እንዳልሆነ ያስባሉ፡፡ የሱስ የኃጢአተኞች ወዳጅ እንደመሆኑ የእነርሱ ወዮታ ልቡን ይነካዋል፡፡ ምንም እንኳ በሰማይም ሆነ በምድር ኃይል ሁሉ የእርሱ ቢሆንም ነገር ግን ሰብዓዊው ፍጡር ደኅንነት የሚያገኝበትየእውነት ብርሃንና ዕውቀት የሚፈነጥቅበትን የአገልግሎት መንገድ ያከብራል፡፡ በዚህም ኃጢአተኞችን ለዚህ ዓለም የብርሃን መተላፊያ መስመር አድርጎ ወደ አነጻት ቤተ ክርስቲያን ይመራል፡፡ —The Acts of the Apostles, P. 122. ChSAmh 23.2

የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ያለማሰለስ የምትሠራቸው—የብርሃን ማዕከሎችን የማቋቋምና ራሳቸውን ለክርስቶስ አገልግሎት አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኞች የሆኑ ነፍሳትን የመባረh ግፍ ሥራዎች ተሰጥቶአት ነበር፡፡ --The Acts of the Apostles, p. 90. ChSAmh 23.3

የፀሐይ ጨረር እጅግ ርቆ የሚገኘውን የምድር ጫፍ ሰርስሮ እንደሚያልፍ ሁሉ፤ የወንጌል ብርሃን በምድር ወዳለ እያንዳንዱ ነፍስ እንዲደርስ አድርጎ እግዚአብሔር ነድፎታል፡፡ የክርስቶስ ቤተ hርስቲያን የጌታችንን ዓላማ አሳhታ ቢሆን ኖሮ በጨለማ በተቀመጡትም ሆነ በሞት ጥላ ስር ባሉት የብርሃን ጸዳል በፈነጠቀ ነበር፡፡ --Thoughts From the Mount of Blessing, p. 42. ChSAmh 23.4

እግዚአብሔር በተትረፈረፈ ጸጋውና ሊደረስበት በማይችል የክርስቶስ ባለጠግነት ከዚህ ዓለም ጋር ሊገናኝ የሚችልበት ሕያው መስመር መሆን ለእያንዳንዱ ሰው የተሰጠው መብትና መልካም ዕድል ነው፡፡ የአዳኙ ፍቅር በሰብዓዊው ፍጡር ተገልጦ የማየትን ያህል ይህ ምድር አጥብቆ የሚሻው ነገር የለም፡፡ መላው ሰማይ ለሰብዓዊው ልብ ደስታና በረከት የሚያስገኘው የተቀደሰ ዘይት መፍሰስ የሚችልበትን መስመሮች እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 419. ChSAmh 24.1

የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ክብርና ሞገስ የክርስቶስ ኃይል ሳይሸሸግ እንዲሠራ ሊያደርግ በሚችለው በአባላቶቿ የተቀደሰ vይወትና ታማኝነት ላይ መተማመን ያደርጋል፡፡ ቅንና ታማኝ ለሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ተጽእኖ ምናልባትም አነስተኛ ግምት ሊሰጥ ቢችልም ነገር ግን ውሎ አድሮ እየተሰማ፣ በስተመጨረሻ የከበረ ሽልማት ባለበት የሚያደርጋቸው ይሆናል፡፡ የጽኑ ቅድስናና የማይናወጥ እምነት ባለቤት የሆነ የእውነተኛ hርስቲያን ብርሃን የሕያውን አዳኝ ኃይል ለዓለም ያረጋግጣል፡፡ ክርስቶስ የዘላለም vይወት እንደሚሰጥ የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ሆኖ ለተከታዮቹ ይገለጣል፡፡ ምንም እንኳ እምብዛም ለዓለም ባይታወቁም--የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከተለመዱት ለየት ያሉ፣ የተመረጡ የደኅንነት ዕቃዎቹና ብርሃን ወደ ዓለም እንዲፈነጥቅ የሚጠቀምባቸው መስመሮቹ ናቸው፡፡ —Review, March 24, 1891. ChSAmh 24.2

የቤተ ክርስቲያን አባላት ሰማያዊው ብርሃን እንዲያንጸባርቅባቸው የሚፈቅዱ ይሁኑ፡፡ መሻታችንን መግዛት ካለመቻልና ከዚህ ዓለም ከንቱ ደስታ በተቃራኒ በቆመ ምስክርነት የዚህን ዘመን እውነት የሚያውጀው ትሁት የጸሎት ድምጽዎ ይሰማ፡፡ ድምጽዎ፣ ተጽእኖዎ፣ ጊዜዎ—እነዚህ ሁሉ ከእግዚአብሔር የተሰጦት እንደመሆናቸው ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፊያነት ጥቅም ላይ መዋል ይኖርባቸዋል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 38. ChSAmh 24.3

የክርስቶስ ደቀ መዝሙሮች በምድር የእርሱ ተወካዮች መሆናቸውን ጌታ አሳይቶኛል፡፡ በግብረገብ ጽልመት በወደቀው በዚህ ምድር ብርሃን እንዲሆኑ ያቀደው እግዚአብሔር በሁሉም አገሮች፣ ከተሞችና መንደሮች ተሰራጭተው እንዲገኙ ዕቅዱ ነው “ለዓለም ሁሉ ለመላእክትም፣ ለሰዎችም ትርዒት ሆነናል”-- Testimonies, vol. 2, p. 63. ChSAmh 25.1

የክርስቶስ ተከታዮች የዓለም ብርሃን እንዲሆኑ ተጠርተዋል፡፡ ሆኖም እንዲያበሩ ጥረት ማድረግ የሚኖርባቸው ራሳቸው እንጂ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ የታይታ መልካምነት ለማሳየት የሚደረግን ማንኛውንም ግብዝ ጥረት አይደግፍም፡፡ ይልቁንም ነፍሶቻቸው በሰማያዊ መርኅዎች እንዲሞሉ ምኞቱ ነው፡፡ ከዓለም ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት በውስጣቸው ያለውን ብርሃን ገልጠው ያሳያሉ፡፡ በእያንዳንዱ የሕይወት ፈርጅ የሚስተዋለው ጽኑና የማያወላውል እምነታቸው የብርሃን ሞገድ መተላለፊያ መስመር ይሆናል፡፡--The Ministry of Healing p. 36. ChSAmh 25.2

ሳውል ጭፍን በሆነ ስህተትና ጥላቻ ተሞልቶ ክርስቶስን ያሳድድ በነበረበት ወቅት ይኸው ያሳድደው የነበረ ክርስቶስ ስለተገለጠለት የዓለም ብርሃን ከሆነችው ቤተ ክርስቲያን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መፍጠር ቻለ፡፡ ሐናንያ ክርስቶስንና በእርሱ _ ቦታ የተሰየሙትን የክርስቶስ ምድራዊ አገልግሎቶች ይወክላል፡፡ የሳውል ዐይኖች ብርሃን እንዲቀበሉ ሐናንያ በክርስቶስ ቦታ ሆኖ ዳሰሳቸው፡፡ በክርስቶስ ፋንታ እጆቹን ጫነበት፣ በክርስቶስ ስም ጸለየለት--ሳውልም መንፈስ ቅዱስን ተቀበለ፡፡ ሁሉም ነገር በክርስቶስ ስምና ሥልጣን ክንዋኔ አገኘ፡፡ ክርስቶስ መሰረት--ቤተ ክርስቲያን ደግሞ መገናኛ ሞገድ ናት፡፡--The Acts of the Apostles, p 122. ChSAmh 25.3

ሐሰት በየቦታው እየተሰራጨ--ታላቁ የነፍሳት ጠላት ኃይሉን እያሰባሰበ ይገኛል፡፡ የሰዎችን አእምሮ እውነት መሳይ በሆኑ ስህተቶች ለማደናገርና ለማጥፋት ይበጀኛል ያለውን እያንዳንዱን መሣሪያ በማቀናጀት ላይነው፡፡ የአምላካዊውን እውነት የተቀበሉ _ ሁሉ ግብረገባዊ ጽልመት በሰፈነበት ድባብ ላይ ሰማያዊው ብርሃን እንዲፈነጥቅ ሊፈቅዱ ይገባል፡፡-Historical Sketches, p. 290. ChSAmh 25.4

የእግዚአብሔር ሕዝቦች በዚህ ዓለም ላይ እንዲያንጸባርቁ ይጠየቃሉ፡፡ ይህን እንዲያደርጉ የተፈለጉት የወንጌል አገልጋዮች ሳይሆኑ እያንዳንዱ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ነው፡፡ ከአንደበቶቻቸው የሚወጡት ቃላት ሰማያዊ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ባላቸው ሕብረት ልባቸው ሐሴት ስለሚያደርግ ለልባቸው ሕይወት የሰጠውን ደስታ በቃላትና በድርጊት ለመግለጽ እውነትን ካላስተዋሉ ጋር ግንኙነት የመፍጠር ምኞት ያድርባቸዋል፡፡ በእነዚህ የዓለም ብርሃን በሆኑ ወገኖች አማካይነት የተሰራጨው ብርሃን አይጠፋም ወይም አይወሰድም::-- Testimonies, vol. 2, pp. 122, 123. ChSAmh 26.1

የክርስቶስ ተከታዮች የሰማያዊ መላእክትን መገኘት የሚያበረታቱ የጽድቅ መሣሪያዎች፣ የወንጌል ሠራተኞች፣ ሕያው አለቶችና ብርሃን አስተላላፊዎች ሊሆኑ ይገባል፡፡ እንደ ቀድሞው ሁሉ የእውነትና የጽድቅ መንፈስ የሚያልፍባቸው መተላለፊያ መስመር እንዲሆኑ ይጠየቃሉ፡፡ Testimonies, vol. 2, pp. 126, 127. ጌታ ቤተ ክርስቲያንን የመለኮታዊ ተጽእኖ ማከማቻ ስፍራ አድርጓታል፡፡ አባላቶቿ ተለውጠው በተራቸው ለምድረ በዳው የጌታ የወይን ተክል የክርስቶስ ጸጋ የሚያልፍባቸው መስመሮች፣ ሕይወት ወደ ዓለም የሚተላለፍባቸው ሞገዶች ሆነው ለመመልከት ሰማያዊው ዩኒቨርስ እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡-- Bible Echo, Aug, 12, 1901, ChSAmh 26.2

ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የፈጠረ ማንኛውም ሰው የብርሃን ጨረር ወደ ሌሎች ይለቃል፡፡ ሆኖም ከብርሃን ምንጭ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሊሰጡ የሚችሉት አንዳችም ብርሃን ሊኖር አይችልም፡ ፡-- Historical Sketches, p. 291. ChSAmh 26.3

የእግዚአብሔር ልጆች ለሌሎች ብርሃን እንዲሆኑ ኃላፊነት ተሰጥቶአቸዋል፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ለሰጣቸው ጥንካሬየወደቀባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን ብለው ነፍሳትን በጽልመት ስህተት ውስጥ ቢተዉ በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ውዳሴና ምስጋና ለክርስቶስ እንድናቀርብ _ እነሆ ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃን ተጠርተናል፡፡Review and Herald, Dec. 12, 1893. ChSAmh 27.1

ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ሁሉ የብርሃን ማስተላለፊያ ይሆናሉ፡፡ የጸጋውን ባለጠግነት ለሌሎች እንዲያደርሱ ወኪሉ ያደርጋቸዋል. . ለሌሎች የሚኖረን አርአያነት አስተማማኝነቱ የሚመሰረተው በምንናገረው ላይ ሳይሆን በማንነታችን ላይ ነው:: ሰዎች የአስተሳሰብ ስልታችንን ሊተቹና ላይቀበሉን ይችላሉ፤ ጥሪያችንንም ችላ ይሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን አድልዎ በሌለው ፍቅር የሚራን ሕይወት ሊያስተባብሉ አይችሉም፡፡ በክርስቶስ ትህትና የተቀረጸ ጽኑ ሕይወት ለዚህ ዓለም ኃይል ነው፡፡-The Desire of Ages, pp. 141, 142. ChSAmh 27.2

የዓለም ብርሃን መሆን ይገባቸው የነበሩ ቢያበሩም—ደካማና የታወኩ የብርሃን ጨረሮች ሆነዋል፡፡ ለመሆኑ ብርሃን ምንድን ነው? ቅድስና፣ መልካምነት፣ እውነት፣ ምኅረት፣ ፍቅር--እውነትን በጸባያችንና በሕይወታችን መግለጥ ነው፡፡ እያንዳንዱ ነፍስ የመልካሙ ሥራ ባለቤት ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር በተወዳጁ ልጁ አማካኝነት ያለውን ሁሉ በመስጠቱ-በብርቱ ኃይል የተሞላው ወንጌል የአማኙን የግል ቅድስና መተማመን ያደርጋል፡፡ እያንዳንዱ ነፍስ ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃን ለጠራን ለእርሱ ያለውን ምስጋና የሚገልጥ ብሩህ እና አንጸባራቂ ብርሃን ሊሆን ይገባል፡፡ እኛ ሁላችን ከእግዚአብሔር ጋር በቅንጅት የተሰለፍን ሠራተኞች ነን፡፡ አዎ--በጌታ የወይን ተክል ሪያ ቅን አገልግሎት የምንሰጥ ሠራተኞች ነን፡፡ በቤተ ክርስቲያኖቻችን፣ በሰንበት ትምህርት ጥናት አባሎቻችንና በጎረቤቶቻችን መሃል መዳን ያለባቸው ነፍሳት አሉ፡፡-Review and Herald, March 24, 1891. ChSAmh 27.3

አማኞች የገዛ ነፍሳቸውን ሕያው አድርገው ማቆየት የሚችሉት ለሌሎች በመሥራት ነው፡፡ ከየሱስ ጋ ተባባሪ ከሆኑ የብርሃን ጨረሮቻቸውከገዛ ወሰኖቻቸው አልፈው ጨለማውን ስለሚሰረስሩ ያለማቋረጥ ብሩህ ሆኖ የሚበራ ብርሃን በቤተ hርስቲያናችን እናያለን፡፡-- Historical Sketches, p. 291. ChSAmh 28.1

“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡:” አይሁዳውያን ደኅንነት ለገዛ ራሳቸው ሕዝብ ጥቅም ብቻ ተወስኖ ይቀራል ብለው አስበው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ክርስቶስ የደኅንነትን ለሁሉም እንደ ጸሐይ ብርሃ መፈንጠቅ አሳይቶአቸው ነበር፡፡ እነሆ መላው ዓለም ይድን ዘንድ ደኅንነት ለሁሉም ተሰጥቶአል፡፡--The Desire of Ages, p. 306. ChSAmh 28.2

የመንፈስ ቅዱስን ተጽእኖ የሚቀበሉ ልቦች የእግዚአብሔር በረከት የሚተላፍባው መስመሮች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ከዓለም ቢወገዱና መንፈስ ቅዱስም ከሰዎች ቢለይ ይህ ዓለም ወና ይሆናል፤ ለጥፋትም ይዳርጋል፤ ይህም የሰይጣን መንግሥት የሥራ ውጤት ነው፡፡ ኃጢአተኞች ባያውቁት ነው እንጂ የዚህን ዓለም በረከት የሚያıኙት የሚንቋቸውና የሚጨቁኑአቸው የእግዚአብሔር ሰዎች በዚህ ዓለም በመኖራቸው ምክንያት ነው፡፡ ነገር ግን ክርስቲያኖች ክርስትናቸው ለማስመሰል ከሆነ ጣዕሙን እንዳጣ ጨው ይሆናሉ፡፡ በዓለም ላይ ምንም ዓይነት በጎ ተጽእኖ አይኖራቸውም፡፡ እግዚአብሔርን በአግባቡ ባለመወከላቸው ከማያምኑ ሰዎች የባሱ ይሆናሉ፡፡--The Desire of Ages, p. 306. ChSAmh 28.3