የክርስቲያን አገልግሎት

138/246

በከተሞች መሥራት

እነሆ ታላቅ ሥራ መሠራት በሚኖርበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ በወንጌል እንደተተነበየው ምድሪቱ አምላካዊውን ቃልተርባለች፡፡ ለተራቡ ነፍሳት የሕይወት እንጀራ ሊሰጥ ይገባል፡፡ ይህን ሥራ ራሱን ለጌታ አገልግሎት ቀድሶ ለሰጠው መንገድ ጠራጊ ከመስጠት የበለጠ የተሻለ ዕድል አይኖርም፡፡ የከበረውን ወቅታዊ እውነት የያዙ በሺ የሚቆጠሩ መጻሕፍት በታላላቅ ከተሞች ነዋሪዎች ቤት ውስጥ ሊገኙ ይገባል፡፡ Southern Watchman, Nov. 20, 1902. ChSAmh 209.1

ለነፍሳትን ደኅንነት መድኅን የሚሆኑ የተባረኩ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች በኅትመት ሥራዎቻችን ቀርበዋል፡፡ መጽሔቶቻችንንም ሆነ ጋዜጦቻችንን በመሸጥ ሥራ ተሳታፊ መሆን የሚችሉ አያሌ ወገኖች አሉ፡፡ እየጠፉ ያሉትን ነፍሳት የማዳን ምኞት እንዲያድርብን ጌታ ጥሪ ያቀርብልናል፡፡ ሰይጣን የተመረጡትን እንኳ ለማሳት በሥራ የተጠመደ እንደመሆኑ ጊዜው በንቃት የምሠራበት ነው፡፡ መጻሕፍቶቻችንም ሆኑ መጽሔቶቻችን የሕዝብ አትኩሮት እንዲያገኙ በማድረግ ወቅታዊውን እውነት የያዘውን ወንጌል ሳንዘገይ ወደ ከተሞቻችን ማዳረስ ይጠበቅብናል፡፡ ተግባራችንን ከግብ ለማድረስ መንቀሳቀስ አይኖርብን ይሆን?— Testimonies, vol. 9, p. 63. ChSAmh 209.2