የክርስቲያን አገልግሎት

1/246

የክርስቲያን አገልግሎት

መግቢያ

ይህ በሁሉም ክርስቲያን ሠራተኞች እጅ እንዲገኝ የምንመኘው መጽሐፍ በተለይ በዕጦትና በችግር ለሚገኙ ወገኖች ለመድረስ የሚረዱንን መመሪያዎች፣ ልዩ አጽንኦት ልንሰጣቸው ለሚገቡ ጉዳዮች፣ በሥራ ላይ ማዋል ስለሚኖርብን ዘዴና ብልሃቶች፣ ትጉዎች ስለሚቀበሉት ሽልማት እንዲሁም ራሱን ለአገልግሎት ቀድሶ የሰጠ የወንጌል ሠራተኛ ሊያደርጋቸው በሚገቡ ጥረቶች ዙሪያ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተጻፉ መልእክቶች ላይ ሰፊ ቅኝት በማድረግ ከተለያዩ መጻሕፍት በጥንቃቄ ተውጣጥቶና ለአንባቢው አመቺነት ባለው መልኩ ተቀናጅቶ የቀረበው ይህ መጽሐፍ ኢንሳይክሎፔዲያ የሚል ስያሜ ቢሰጠው የሚያንሰው እንጂ የሚበዛበት አይሆንም፡፡ ChSAmh 5.1

ከክርስቲያን አገልግሎት ጽንሰ ሐሳብ ስፋትና ጥልቀት አኳያ በዚህ መጽሐፍ የሰፈሩት ጽሑፎች በትንቢት መንፈስ የቀረቡትን የዘርፉን ርዕሰ ጉዳዮች እንዳለ አለማካተታቸው እሙን ቢሆንም፤ ወደ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ለመምራት የሚያስችል በቂና አስተማማኝ ኃይል አላቸው፡፡ ይህ መጽሐፍ ክርስቲያኑ ሠራተኛ በወይኑ ተhል ዙሪያ አገልግሎቱ እውነትን እየቆፈረና ዘመናዊነት የተላበሱ ሳይንሳዊ አሠራሮችን ጥቅም ላይ እያዋለ ነፍሳትን ለክርስቶስ ለማሸነፍ ያስችለዋል፡፡ ChSAmh 5.2

ይvን መልእhት ከተለያዩ መጻሕፍት የማውጣጣት ሥራ ሲሠራ በደራሲዋ የተገለጸውን በአግባቡ የተሰደረ ጽንሰ ሐሳብ ጠብቆ ለማስፈር ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎአል፡፡ እነዚv ከተለያዩ መጻሕፍት ተውጣጥተው የቀረቡ ጽሑፎች በሁሉም የአገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ የወንጌል ChSAmh 5.3

አገልጋዮችና የሥራ መሪዎች እንዲሁም “ዘመኑን የተረዱና እስራኤላውያንም ምን ማድረግ እንደሚገባቸው የተገነዘቡ” ልባቸው በታላቁ የወንጌል ተልዕኮ መንፈስ ለተነካ ወንዶችና ሴቶች በዋጋ የማይተመን ጠቀሜታ ይኖራቸዋል የሚል ጽኑ ተስፋ አለ፡፡ ChSAmh 6.1

በዚህ አጋጣሚ ለጀነራል ኮንፈረንስ የቤትና ቤተሰብ ዘርፍ ግብረ ኃይል፣ በተለያዩ መጻሕፍት የሰፈሩትን ሐሳቦች በማንበብና ተስማሚ የሆኑትን ነቅሶ የማውጣት ሥራ በሥራት ይህን መድብል እውን ላደረጉ ሌሎች ክርስቲያን ሠራተኞች፣ እንዲሁም ለሥራው ምሉዕነት ልባዊ አስተያየታቸውንና ድጋፋቸውን ለሰጡ ሁሉ የከበረ ምስጋናችን ይደረሳቸው፡፡ ChSAmh 6.2

GENERAL CONFERENCE HOME MISSIONARY DEPARTMENT