የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ከበላይ ላሉ ሰዎች ከፍተኛ ደሞዝ ለመክፈል ሀሳብ ቀረበ
በሌሊት ጊዜ በፊቴ ከቀረቡ እይታዎች የተነሳ ልቤ በጥልቅ ታውኳል፡፡ በሌሊት ጊዜ ከአንዳንድ ወንድሞቼ መስማማት የማልችልባቸውን ሀሳቦች ሰማሁ፡፡ የተናገሯቸው ዓረፍተ ነገሮች በስህተት መስመር ላይ መሆናቸውንና ከማታለያ የሚጋርዳቸው ልምምድ እንደሌላቸው ያሳያሉ፡፡ ከአንዳንድ ወንድሞች ከናፍር በእግዚአብሔር ማመንንም ሆነ ለእውነቱ ታማኝነትን የማያሳዩ መግለጫዎችን በመስማቴ አዝኛለሁ፡፡ ሥራ ላይ ቢውሉ ኖሮ ከቀጭኗና ከጠበበችው መንገድ የሚያርቁ ሀሳቦች ቀርበው ነበር፡፡ Amh2SM 186.3
አንዳንዶች ከፍ ያሉ መክሊቶች ላሉአቸው ሰዎች ከሌሎች ከፍ ያለ ደሞዝ ቢከፈላቸው ኖሮ እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር አብረው ይቆዩ ነበር ብለው ያስባሉ፤ እንዲህ ቢሆን ደግሞ ብዙ ሥራ በተሟላ ሁኔታ ይሰራና የእውነት ሥራ በበለጠ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ይቆም ነበር ብለው ያስባሉ፡፡ Amh2SM 186.4
ይህን ጥያቄ በተመለከተ በፍጹም ከማይሳሳተው መመሪያ ተቀብያለሁ፡፡ ይህ እቅድ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ «ትክክለኛ የሆነ ጠቃሚነትን እና እንደ እርሱ ያሉ ሰራተኞች የሚኖራቸው ተጽእኖ ምን መሆን እንደሚችል የሚያውቅ ማን ነው? ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ የሌላ ሰውን ጠቃሚነት ለመወሰን ማንም ሰው ብቃት የለውም፡፡ Amh2SM 186.5
አንድ ሰው የያዘው ሥልጣን ወይም ሀላፊነት ብቻውን ሰውዬው በእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ጠቃሚነት እንዳለው አያመለክትም፡፡ ለመልካም ነገር ተጽእኖ እንዲኖረው የሚያደርገው በመንፈስ ቅድስና አማካይነት የሚመጣው ክርስቶስን መሰል ባሕርይ ማጎልበት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ግምት አንድ ሰው የሚሰጠውን አገልግሎት ዋጋ የሚወስነው ያለው የታማኝነት መጠን ነው፡፡ Amh2SM 186.6
እግዚአብሔር አገልግሎታቸውን የሚቀበለው የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች የሆኑትን ብቻ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ ሰው ምንም ነገር ማድረግ አይችልም፡፡ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር ከፍ ባለ ሥፍራ የሚያስቀምጠው ለእግዚአብሔርና ለሰው ያለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ለመለኮታዊ ትዕዛዝ ታዛዥ መሆን ከእግዚአብሔር ጋር አብረን ሰራተኞች እንድንሆን ያስችለናል፡፡ ፍቅር በክርስቲያን ዛፍ ላይ የሚፈራ ፍሬ፣ ለአህዘብ ፈውስ እንደሆነው የሕይወት ዛፍ ቅጠሎች ያለ ፍሬ ነው፡፡--Manuscript 108, 1903. Amh2SM 187.1