የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

134/349

ክፍል 5—የሰራተኞቻችን ክፍያ

መግቢያ

ለአገልግሎት የሚሰጥ ክፍያ ጉዳይ ለእያንዳንዱ ሰው የማያቋርጥና ተግባራዊ ፍላጎት ነው፡፡ በጊዜው ባሉ በርካታ የኤለን ኋይት መጻሕፍት ውስጥ በደንብ የተወከለ ርዕስ ነው፡፡ {2SM 172.1} Amh2SM 172.1

በዚህ ቦታ የቀረቡት የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ሰራተኞችን ክፍያ በተመለከተ ገዥ የሆኑ መርሆዎችን ለመከለስ በጄኔራል ኮንፍረንስ የተሰየሙ አንዳንድ ኮሚቴዎች የሚያደርጉትን ጥናት እንዲረዱ የተሰባሰቡ ተጨማሪ ምክሮች ናቸው፡፡ እነዚህ ማስረጃዎች ለኮሚቴው ጠቃሚነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን እነርሱ በሰጡት አስተያየት መሰረት እዚህ እየተካተተ ነው፡፡ {2SM 172.2} Amh2SM 172.2

የእነዚህና ሌሎች ከተለያዩ ሰነዶች እና የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ሰራተኞች ከሚሰሩት ድርጅት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ ከተሰጡ ምክሮች የተወሰዱ መርሆዎች ክለሳ ትርፋማ በሆነ ሁኔታ ይነበባል፡፡ {2SM 172.3} Amh2SM 172.3

ገንዘብን ከሚመለከቱ ጫናዎች የተነሳ ከእግዚአብሔር ሥራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ከሌላቸው የስራ መስመሮች ትልቅ ገቢ የሚያስገኝ ሥራን ለመስጠት የሚመጡ ግብዣዎችን ለመቀበል የሚፈተነውን ማንንም በተመለከተ «ገንዘብን ከሚመለከቱ ምክንያቶች የተነሳ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመልቀቅ እየወሰነ ለነበረ ሰው የተሰጠ ምክር” የሚለው ምዕራፍ የተግዳሮትና የሚያቀዘቅዙ ሀሳቦችን ይሰጣል፡፡ በእነዚህ የኤለን ኋይት መልእክቶች ውስጥ የመስዋዕትነት መንፈስ የሆነው የክርስቶስ መንፈስ ዋና ሀሳብ ነው፡፡ --. {2SM 172.4} Amh2SM 172.4

White Trustees

[በጥር 4 ቀን 1906 ዓ.ም በወጣው ሪቪው ኤንድ ሄራልድ በሚል መጽሔት ላይ የወጣ) {2SM 172.5}