የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
የታማኝነት ሽልማት
በልብህ ውስጥ ከክፉ ኃይል ጋር ታላቅ ግጭት ይገጥምሃል፡፡ ከፍ ያለ ሥራ እንደነበረህ ተሰምቶሃል፣ ነገር ግን በምንም መንገድ ቢሆን ራስህን ከፍ ማድረግን ሳትፈልግ በመንገድህ ላይ በቀጥታ የተቀመጠልህን ሥራ ብትቀበልና በታማኝነት ብትፈጽመው ኖሮ በምድራዊ ጦርነት አሸናፊዎች የሆኑ ሰዎች ከሚያገኙት የበለጠ ንጹህ፣ የበለጸገ እና የሚያረካ ሰላምና ደስታ ለነፍስህ ይመጣልህ ነበር፡፡ ለእግዚአብሔር መኖርና መስራት እንዲሁም ያለውን ጊዜና ችሎታ ሁሉ በምንችለው መጠን በደንብ መጠቀም በጸጋና በእውቀት ማደግ ነው፡፡ ይህ ሥራችን ስለሆነ ማድረግ እንችላለን፡፡ በእርግጥ በሥራህ የተከናወነልህ ለመሆን ጥርጣሬ ያለባቸውን ጥያቄዎችን ማስወገድና ከመለኮት በተሰጠህ ተልእኮ እውነታ ሙሉ እምነት ሊኖርህ ያስፈልጋል፡፡ {2SM 168.1} Amh2SM 168.1
የአገልግሎትህ ደስታ፣ ስኬትና ክብር ለጌታ ጥሪ «እነሆ እዚህ አለሁ፤ እኔን ላከኝ” (ኢሳ.6፡8) ብለህ ለመመለስ በሚያዳምጡ ጆሮዎች ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን ነው፡፡ ጌታ ሆይ፣ በልቤ ከሁሉ ይበልጥ ቅዱስ በሆነ ፍቅር እዚህ ነኝ፤ አእምሮዬን ንጹህና ክቡር ከሆኑ ሀሳቦቹ ጋር ውሰድ፣ ውሰደኝና ለአገልግሎትህ ብቁ አድርገኝ፡፡ {2SM 168.2} Amh2SM 168.2
በተቻለ ፍጥነት አሁን ወደ ኋላ እንድትመለስ እማጸንሃለሁ፤ እግዚአብሔር የሰጠህን ተልእኮ ተቀበልና ተልእኮህን ለመቀደስ ንጽህናንና ቅድስናን ፈልግ፡፡ አትዘግይ፤ በሁለት ሀሳቦች መካከል አትቁም፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከሆነ እርሱን አገልግል፤ ነገር ግን በኣል አምላክ ከሆነ እርሱን አገልግል፡፡ ከባድ በሆነ የስቃይ ትምህርት ቤት እንደ አዲስ መማር ከፈለግክ በእግዚአብሔር የመታመን አሮጌ ትምህርት አለልህ፡፡ ዲ. ኤም ካንራይት በኢየሱስ እንዲዋጥ ፍቀድለት፡፡. . . {2SM 168.3} Amh2SM 168.3
በአጭር ጊዜ ውስጥ ስሞቻችን ሊጠሩና ማንም መልስ የሚሰጥ ላይኖር ይችላል፡፡ ያ ሕይወት በእግዚአብሔር እንዲደበቅና ስምህ በሰማይ ተመዝግቦ ዘላለማዊ እንዲሆን ፍቀድ፡፡ ክርስቶስ በሚመራህ መንገድ ሁሉ ተከተለው፣ በጊዜ አሸዋ ላይ ከኋላህ የምትተዋቸው ዱካዎችህ ሌሎች በቅድስና መንገድ ላይ ያለ አደጋ ሊከተሉአቸው የሚችሉአቸው ይሁኑ፡፡ {2SM 168.4} Amh2SM 168.4
ወደ ሞት በሚመራው መንገድ ሁሉ ላይ ስቃይና ቅጣት፣ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ፣ እንዳይሄዱበት ከእግዚአብሔር መልእክተኞች የሚመጡ ማስጠንቀቂያዎች ስላሉበት፣ እግዚአብሔር ይህን መንገድ ሥርዓት ለሌላቸውና ሀሳበ ግትሮች እንኳን ራሳቸውን ለማጥፋት ከባድ ያደርግባቸዋል፡፡ ወደ ዘላለም ሕይወት በሚመራው ቀጥ ያለ መንገድ ላይ የደከሙትን ለማበርታት የደስታ ምንጮች አሉ፡፡ እውነተኛና ጠንካራ የሆነ የነፍስ ደስታ የሚጀምረው የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ በውስጥ ሲመሰረት ነው፡፡ አሁን እግዚአብሔር የሚመራውን መንገድ ከመረጥክ እና የተግባር ድምጽ ወደሚጠራበት ብትሄድ ሰይጣን በፊትህ አጉልቶ ያሳያቸው ችግሮች ይጠፋሉ፡፡ {2SM 169.1} Amh2SM 169.1
በተከተሉት መጠን እየጠራና እየጸና ከሚሄደው መንገድ ሌላ መንገድ ደህንነት የሌለበት ነው፡፡ ደህነት ባለበት መንገድ ላይ አንዳንዴ እግር ሊንሸራተት ይችላል፡፡ ያለ ፍርሃት ለመራመድ እጅህ በክርስቶስ እጅ በደንብ መያዙን ማወቅ አለብህ፡፡ ለአንድአፍታ እንኳን አደጋ እንደሌለ አድርገህ አታስብ፡፡ ጠቢባን እንኳን ስህተቶችን ይፈጽማሉ፡፡ ብርቱዎች እንኳን አንዳንድ ጊዜ ተደናቅፈው ይወድቃሉ፡፡ ሞኞች፣ በራሳቸው የሚተማመኑ፣ በስሜት የሚነዱ፣ ደስ ባላቸው ጊዜ መንገዳቸውን መለወጥ እንደሚችሉ በመናገር ራሳቸውን በማታለል ያለ ሀሳብ ወደ ፊት የሚገፉ ሰዎች ወጥመድ ባለበት መንገድ ላይ እየሄዱ ናቸው፡፡ ከወደቁበት ስህተት ሊያገግሙ ይችላሉ፣ ነገር ግን አንድ የስህተት እርምጃ በመሄዳቸው የዘላለም ጥፋታቸውን እርግጠኛ የሚያደርጉ ስንቶች ናቸው፡፡ {2SM 169.2} Amh2SM 169.2
በሌላ መንገድ ልታገኛቸው የማትችላቸውን ነገሮች ለማግኘት ስትል አስተያየትን የመሸሸግን ፖሊሲ ከተጫወትክ፣ ባለመሰልቸት፣ በልፋት እና በጦርነት መሸነፍ ያለበትን ነገር በብልጠትና በተንኮል ካገኘህ፣ ራስህ በሸመንከው መረብ ውስጥ ተጠላልፈህ ከዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ከወደፊቱ ሕይወትም ትጠፋለህ፡፡ {2SM 169.3} Amh2SM 169.3
የእምነት መርከብህ በዚህ ቦታ መሰበርን እግዚአብሔር ያርቀው፡፡ ጳውሎስን ተመልከት፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ እኛ ጊዜ የሚያስተጋቡትን የእርሱን ቃላት አድምጥ፡- «መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም” (2ጢሞ.4፡7፣8)፡፡ ከጳውሎስ የሚወጣው ድል የሚያስገኝ የጦርነት ጩኸት እዚህ አለ፡፡ የአንተ ምን ይሆን ይሆን? {2SM 169.4} Amh2SM 169.4
ኤልደር ካንራይት፣ አሁን ለነፍስህ ብለህ የእግዚአብሔርን እጅ እንደገና አጥብቀህ እንድትይዝ እለምንሃለሁ፡፡ ከዚህ የበለጠ ለመጻፍ ደክሞኛል፡፡ እግዚአብሔር ከሰይጣን ወጥመድ ያድንህ የሚለው ጸሎቴ ነው፡፡--Letter 1, 1880. {2SM 170.1} Amh2SM 170.1