የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ክርስቶስ ምሳሌ የሆነ ሰው
የክርስቶስ ሕይወት ምን ዓይነት ሕይወት ነበር? ክርስቶስ አናጺ ሆኖ በለፋ ጊዜና ከዓለም የታላቁን መለኮታዊ ተልእኮ ምስጢር በደበቀ ጊዜ፣ ልክ ነጭ አረፋ ይደፍቅ በነበረው በገሊላ ባሕር ላይ በሄደ ጊዜ፣ ወይም ሙታንን ከሞት ባስነሳ ጊዜ፣ ወይም መላውን ሰብዓዊ ዘር ወደ አዲስና ፍጹም ሕይወት ለማንሳት በመስቀል ላይ ለሰው መስዋዕት ሆኖ በሞተ ጊዜ ምሳሌ የሆነ ሰው በመሆን ተልእኮውን በእርግጠኝነት እየፈጸመ ነበር፡፡ የእርሱ ሕይወት ትምህርት ወንዶችና ሴቶች ተራ በሆነ በእለታዊ የሕይወት ጉዞ እንኳን ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት በቅርበት መጓዝ እንዳለባቸው እንዲያስተምር ኢየሱስ ክብር ሳያገኝና ሳይታወቅ በናዝሬት ረዥም ጊዜ ኖረ፡፡ ይህ የሰማይ ንጉስ ከእኛ እንደ አንዱ ለመሆን ፈቃደኛ መሆን እንዴት ያለ ውርደት እና ምንኛ ራስን ዝቅ ማድረግ ነው፡፡ ለሁሉም መራራት በመቻሉ የልቦችን ሁሉ ርኅራኄ ሳበ፡፡ የናዝሬት ሰዎች ጥያቄ ባዘለ ጥርጣሬ እንዲህ በማለት ጠየቁ፣ «ይህ ጸራቢው» (ማር. 6፡3)፣ የዮሴፍና የማርያም ልጅ አይደለምን? {2SM 163.3} Amh2SM 163.3
ተራ ሥራ የነበራቸው ተራ ሰዎች መላእክትን በእኩለ ቀን ከተገናኙበት ጊዜ፣ ወይም በቤተልሄም ሜዳዎች እረኞች መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ የሰማይ ሰራዊትን ዝማሬዎች ከሰሙበት ጊዜ ይልቅ ዛሬ ሰማይና ምድር አልተራራቁም፡፡ በእግዚአብሔር ዓይን ትልቅ የሚያደርግህ ወደ ታዋቂነት ደረጃ ለመድረስ መፈለግህ አይደለም፣ ነገር ግን የሰማይ መላእክት ልዩ ጥበቃ እንዲያደርጉልህ የሚያደርገው መልካምነት ያለበት ትሁት ሕይወት እና የታማኝነት ሕይወት ነው፡፡ ምሳሌ የሆነው ሰው፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን እንደ መቀማት ያልቆጠረው፣ በራሱ የእኛን ተፈጥሮ ወሰደና ወደ ሰለሳ የሚጠጉ ዓመታትን በኮረብታዎች መካከል ተሰውሮ በተሰወረ የገሊላ ከተማ ኖረ፡፡ የመላእክት ሰራዊት በሙሉ ይታዘዙት ነበር፣ ነገር ግን ታላቅ ወይም ከፍ ያለ እንደሆነ አድርጎ ራሱን አላየም፡፡ ራሱን ለማስደሰት በስሙ ላይ «ፕሮፌሰር» የሚል ቅጥያ አልጨመረበትም፡፡ ተከፍሎት የሚሰራ፣ ለሚሰራላቸውም አገልጋይ የነበረ አናጺ ነበር፡፡ በዚህ ድርጊቱ ሰማይ እጅግ ቅርብ የሚሆንልን ተራ በሆነ የሕይወት እንቅስቃሴ መሆኑንና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሚመጡና የሚሄዱ ሰዎችን እርምጃዎች ሀላፊነት ከሰማይ ጉባኤ የሚላኩ መላእክት እንደሚወስዱ አሳየ፡፡ {2SM 164.1} Amh2SM 164.1
ኦ፣ የክርስቶስ መንፈስ ተከታዮቹ ነን በሚሉ ላይ ምነው ባረፈ! ክርስቶስ በሕይወቱ የሰጠን ትምህርት የሥራና የልፋት ስለሆነ ሁላችንም ለመስራትና ለመልፋት ፈቃደኞች መሆን አለብን፡፡ ማንም ጥሩ ሰርተሃል ብሎ የሚያመሰግን በሌለበት ሥራህን በንጽህናና በታማኝነት በመስራት ተራ በሆኑ ነገሮች ለእግዚአብሔር ኖረህ ቢሆን ኖሮ አሁን ባለህበት ቦታ አትሆንም ነበር፡፡ መልካም ቃላትን በጥበብ በመናገር፣ አስበህ የቸርነት ሥራን በመስራት፣ በየቀኑ የዋህነትን፣ ንጽህናን እና ፍቅርን በመግለጥ ሕይወትህን የታማኝነት ሕይወት ማድረግ ትችላለህ፡፡ ካለህ ብርሃን አንጻር ሲታይ የመጨረሻ እርምጃ እንደወሰድክ ይሰማኛል፡፡ ለሰይጣን እያንዳንዱን እድል ሰጥተሃል፡፡ {2SM 164.2} Amh2SM 164.2