የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ቀዝቃዛ የሆነ ሥርዓታዊነት ወይስ ወግ አጥባቂነት
ሥርዓት፣ ዓለማዊ ጥበብ፣ ዓለማዊ ሕብረት፣ ዓለማዊ መምሪያ ለብዙዎች የእግዚአብሔር ኃይል ይመስላቸዋል፣ ነገር ግን ተቀባይነት ሲያገኝ በማስጠንቀቂያዎች፣ በተግሳፆች እና በምክሮች ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ብርሃን ወደ ዓለም እንዳይመጣ ለመከልክል እንቅፋት ሆኖ ይቆማል፡፡ {2SM 19.3} Amh2SM 19.3
በታላቅ ኃይል መታወጅ ካለበት የሦስተኛው መልአክ መልእከት ሰዎችን ለማራቅ እሱ [ሰይጣን] ባለው የማግባባትና የማታለል ኃይሉ ሁሉ እየሰራ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን እየባረከ መሆኑንና የእሱን ማታለያዎች ለይተው ማወቅ እንዲችሉ እያዘጋጃቸው እንደሆነ ሰይጣን ሲያይ የነፍሳትን መከር መሰብሰብ እንዲችል በአንድ በኩል ወግ አጥባቂነትን ለማምጣት እና በሌላ በኩል ደግሞ ቀዝቃዛ ሥርዓታዊነትን ለማምጣት ዋና ኃይሉን በመጠቀም ይሰራል፡፡ ያለመታከት ነቅተን መጠበቅ ያለብን ዘመን አሁን ነው፡፡ ነቅታችሁ ጠብቁ፣ ሰይጣን በመካከላችሁ ትንሽ እንኳን እንዲንቀሳቀስ የሚያደርገውን መንገድ ዝጉ፡፡ {2SM 19.4} Amh2SM 19.4
በግራና በቀኝ ራሳችንን መጠበቅ ያለብን አደጋዎች አሉ፡፡ ማበረታቻ የሚያስፈልጋቸውና በፊታቸው ትክክለኛ ምሳሌ ልናስቀምጥላቸው የሚገባ ልምድ የሌላቸውና ወደ እምነቱ ገና አሁን የመጡ አዳዲስ ነፍሳት ይኖራሉ፡፡ አንዳንዶች ጽድቅ በእምነት አስተምህሮን በትክክል አይጠቀሙትም፡፡ ወደ አንድ ጎን ባጋደለ መልኩ ያቀርቡታል፡፡ {2SM 20.1} Amh2SM 20.1
ሌሎች ደግሞ በትክክል ያልቀረቡትን ሀሳቦች በመያዝ ሥራን ሙሉ በሙሉ ችላ በማለት ምልክቱን በግልጽ አልፈው ይሄዳሉ፡፡ {2SM 20.2} Amh2SM 20.2
ትክክለኛ እምነት ሁልጊዜ በፍቅር ይሰራል፡፡ ወደ ቀራኒዮ ስትመለከቱ ሳለ ነፍሳችሁ ተግባሯን ትታ ጸጥ እንድትል፣ ራሳችሁን ለእንቅልፍ እንድታዘጋጁ ሳይሆን ነፍስን ከራስ ወዳድነት ቆሻሻ በማንጻት የሚሰራ እምነትን፣ በክርስቶስ ማመንን እንዲፈጥርላችሁ ነው፡፡ ክርስቶስን በእምነት ስንጠማጠመው ሥራችን ተጀምሯል፡፡ እያንዳንዱ ሰው በብርቱ ጦርነት ማሸነፍ ያለበት ክፉና ኃጢአተኛ ልምዶች አሉበት፡፡ እያንዳንዱ ነፍስ የእምነትን ገድል እንዲጋደል ይጠበቅበታል፡፡ ሰው የክርስቶስ ተከታይ ከሆነ ለሌሎች ያለው አያያዙ ጭካኔ ያለበት ሊሆን አይችልም፣ ርኅራኄ የሌለው ልበ-ደንዳና መሆን አይችልም፡፡ ንግግሩ ሸካራ አይሆንም፡፡ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በጉረኝነት የተሞላ አይሆንም፡፡ የሌሎችን ሀሳብ የሚያጣጥል ወይም ጎጂ የሆኑ ቃላትን በመጠቀም የሚገስጽና የሚኮንን አይሆንም፡፡ {2SM 20.3} Amh2SM 20.3
የፍቅር ሥራ የሚመነጨው ከእምነት ሥራ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት ማለት የማያቋርጥ ሥራ ማለት ነው፡፡ «መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን ያከብሩ ዘንድ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰዎች ሁሉ ፊት ይብራ” (ማቴ. 5፡ 16)፡፡ የእርሱን በጎ ፈቃድ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሰራ እግዚአብሔር ስለሆነ መዳናችሁን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ፈጽሙ፡፡ ለበጎ ሥራ የምንቀና መሆን አለብን፣ መልካሙን ሥራ እንዲቀጥል ለማድረግ መጠንቀቅ አለብን፡፡ እውነተኛው ምስክር «ስራህን አውቃለሁ” ይላል (ራዕይ 2፡2)፡፡ {2SM 20.4} Amh2SM 20.4
እኛ የምንፈጽማቸው በርካታ ተግባራት በራሳቸው መዳናችንን ባያረጋግጡልንም ከክርስቶስ ጋር አንድ የሚያደርገን እምነት ነፍስን ለተግባር ያነሳሳል፡፡ {2SM 20.5} Amh2SM 20.5
በእግዚአብሔር ፍቅር መሆን አለመሆናቸውን ለማወቅ በየቀኑ ራሳቸውን ለመመርመር እና ራሳቸውን በብርሃን መስመር ላይ ለማስቀመጥ ለነፍሶቻቸው ትኩረት ለመስጠት ጊዜ የሌላቸው ሰዎች ለሰይጣን አስተያየቶችና እቅዶቹን ለመፈጸም የሚሰጡት ጊዜ ይኖራቸዋል፡፡ {2SM 20.6} Amh2SM 20.6
ሰይጣን ለራሳቸው ቦታን ሲያዘጋጁ እየሰፉ የሚሄዱ ትንንሽ ሽብልቆችን በመጠቀም ራሱን ያቀርባል፡፡ በዚህ ጊዜ የሰይጣን የማይረቡ ዘዴዎች ልዩ በሆነ የእግዚአብሔር ሥራ ውስጥ ይመጣሉ፡፡ --Manuscript 16, 1890. {2SM 21.1} Amh2SM 21.1