የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

116/349

ክፍል 4—ለሠራተኞች ምክሮች

መግቢያ

በማስታወሻ ደብተር ቅጠሎች ላይ የታዩት በርካታ ጠቃሚ መልእክቶች በተለየ ሁኔታ የተላኩት ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ሰራተኞች ነበር፡፡ በቅርቡ በወጡ ሌሎች የኤለን ኋይት መጸሕፍት ውስጥ ያልተጠቃለሉት ወይም ያልተጠቀሱት እንደ እነዚህ ያሉ ምክሮች በዚህ እትም ውስጥ ተካትተዋል፡፡ አንባቢው እነዚህ መልእክቶች በአገልግሎት ውስጥ እና መክሊቶቻቸውን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ቀድሰው በሰጡ ሁሉ ዘንድ ልዩ ትኩረት የሚሹ ርዕሶችን እንደሚነኩ ይገነዘባል፡፡ {2SM 146.1} Amh2SM 146.1

የዚህ ክፍል የመዝጊያ ምዕራፍ የተጻፈው በመሪዎችና በፈቃደኛ አገልግሎት ዘንድ እምነት አትርፎ ለነበረና ተወዳጅ ለነበረ፣ ነገር ግን በመጨረሻ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግንኙነት እስኪያቋርጥ ድረስ በልቡ ውስጥ ትንሽ እምነት የማጣትና የመራርነት ዘር እንዲበቅል ለፈቀደ ለዲ. ኤም. ካንራይት ነው፡፡ ዲ ኤም ካንራይት ይህን ከማድረጉ በፊት አገልግሎትን ትቶ በመውጣት ቢያንስ ሶስት ጊዜ ተመልሷል፡፡ ሚስስ ኋይት ካንራይትን ለመያዝ በተደጋጋሚ ሞክራለች፡፡ የዚህ ዓይነት አንድ ተማጽኖ እዚህ ቀርቧል፡፡ ሌሎች በርካታ ግንኙነቶችን በተመለከተ ማጣቀሻዎች ከዚህ ምዕራፍ በተገናኘ ሁኔታ ይገኛሉ፡፡ {2SM 146.2} Amh2SM 146.2

ካንራይት በ1887 ዓ.ም ከሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረውን ግንኙነት ለዘላለም አቋረጠ፡፡ በቀረው የሕይወት ዘመኑ ቤተ ክርስቲያንን እና ኤለን ኋይትን በመቃወም ሲናገርና ሲጽፍ አሳለፈ፡፡ በዚህ ክፍል መዝጊያ ላይ ለእሱ የቀረበው ልባዊ ተማጽኖ እያንዳንዱ ሰው ራሱን በደንብ እንዲመረምር ጥሪ ያቀርባል፡፡ -- {2SM 146.3}. Amh2SM 146.3

White Trustees.