የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ክፍል 3—ብልህ ያልሆኑ ግንኙነቶች
መግቢያ
ቀድሞ በአውስትራሊያ ባደረገችው ጉዞ ወቅት (1891-1900) ኤለን ኋይት የማተሚያ ቤታችን እውቅ ሰራተኛ ለነበረና የምስጢር ማህበራት ከሚያደርጓቸው ነገሮች ጋር ጥልቅ ግንኙነት ለነበረው ሰው ምክር እንድትሰጥ ተጠርታ ነበር፡፡ ይህ ወንድም ምንም እንኳን በማህበሩ ውስጥ ከፍተኛ የክብር ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም የሰጠችው ምክር ከምስጢር ማህበራት ጋር የነበረውን ግንኙነት እንዲያቋርጥ መራው፡፡ {2SM 120.1} Amh2SM 120.1
ሚስስ ኋይት ሳትኮንነው ክርስቲያን ሁለት ጌቶችን ማገልገል ወይም ለሁለት ሥልጣናት መገዛት እንደማይችል አመለከተች፡፡ በምስጢር ማህበራት ተግባራት ውስጥ ከነበረው ተሳትፎ የተነሳ ለቤተ ክርስቲያን ይሰራ የነበረው ሥራ በሚያሳዝን ሁኔታ ችላ ተብሎ የነበረው ወንድማችን በኤለን ኋይት ምክሮች ውስጥ ለመረዳት የማይከብድ እውነትን አገኘ፣ ሚስስ ኋይት እራሷም በማታውቀው ሁኔታ የምስጢር ማህበራት አባላት ብቻ የሚጠቀሙበትን የምስጢር ምልክት በመስጠቷ በመልእክቱ ላይ ያለው እምነት ጸና፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከምስጢር ማህበሩ ጋር ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ምንም ነገር ሊያናጋ እንደማይችል ማረጋገጫ ቢሰጠውም ከምስጢር ማህበራት ጋር የነበረውን አባልነት ወዲያውኑ ተወ፡፡ ከአመታት በኋላ ይህንን ልምምድ ወደ ኋላ በመመልከት የትንቢት መንፈስ መልእክት ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ መለወጡን መሰከረ፡፡ {2SM 120.2} Amh2SM 120.2
በዚህ ጊዜና ከዚህ ጋር በተገናኘ ሁኔታ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች እነዚህን ከሚመስሉ ድርጅቶች ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት ሚስስ ኋይት በተሟላ ሁኔታ ጽፋለች፡፡ ይህ ሀሳብ «ክርስቲያኖች የምስጢር ማህበራት አባል መሆን አለባቸውን?” በሚል ርዕስ ታትሟል፡፡ በመጽሔት መልክ በአውስትራሊያና በዩናይትድ እስቴትስ በሰፊው ተሰራጭቷል፣ ነገር ግን ከሕትመት ውጭ ከሆነ ረዥም ጊዜ ሆኖታል፡፡ ይህ መጽሔት ሙሉ በሙሉ በዚህ ቦታ እንደገና ታትሟል፡፡ {2SM 120.3} Amh2SM 120.3
ሁለተኛው ምዕራፍ የሰራተኛ ማህበራትን በተመለከተ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ሊኖራቸው ስለሚገባ አመለካከት ከሚስስ ኋይት ብዕር ምክሮችን ይዟል፡፡ ይህ ነገር ካንትሪ ሊቪንግ በሚል መጽሔት ክፍል ሁለት ሆኖ በ1946 ዓ.ም ታትሞ ነበር፡፡ በዚህ ቦታ ቋሚ በሆነ መልክ ቀጣይነት ላለውና በጸሎት ለሚደረግ ጥናት ተጽፎ ይገኛል፡፡ የኋይት ጽሁፎች ባለ አደራዎች፡፡ {2SM 120.4} Amh2SM 120.4