የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

84/349

ምዕራፍ 12—ሶስቱ መላእክትና ሌላኛው መልአክ

[ብዙ ጊዜ ከስህተት ትምህርቶችና ከስህተት እንቅስቃሴዎች ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ መሪ የሆነ ሰው መልእክቱንና ስራውን ከራዕይ 18፡1 ጋር ያመሳስላል፡፡ አንዳንድ የስህተት ትምህርቶች በየዘመናቱ በራዕይ 14 ላይ ያለውን የሶስቱን መላእክት መልእክትንም አካትተዋል፡፡ የዚህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ ቀጥለው ባሉ ግንኙነቶች የተገለጸና ሚስስ ኋይት በ1896ዓ.ም የተጋፈጠችው ነው፡፡ ረዥም ቢሆኑም እንኳን የሶስቱን መላእክት መልእክት በሰፊ ስራቸው መመርመር ከሚያጠናክሩ አረፍተ ነገሮች የተነሳ እንደ ትልቅ ሀብት ሊቆጠሩ ይችላሉ፡፡ አሰባሳቢዎች] {2SM 101.1} Amh2SM 101.1