የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
«በሕግና በምስክር” የተፈተነ
በእነዚህ አሳሳች ቀናት ውስጥ እያንዳንዱ በእውነት የጸና ሰው ለቅዱሳን ስለተሰጠው እምነት መከራከር አለበት፡፡ ቢቻለው ኖሮ የተመረጡትን እንኳን ሊያስታቸውና ከእውነት ሊመልሳቸው እያንዳንዱ የስህተት አይነት ምስጢራዊ በሆነ በሰይጣን አሰራር ይመጣል፡፡ መጋፈጥ የሚያስፈልገን ሰብዓዊ ጥበብ ይኖራል፡፡ ይህ ጥበብ ፈሪሳውያን እንደነበሩት ሁሉ የእግዚአብሔር ሕግ መምህራን የሆኑ የተማሩ ሰዎች ጥበብ ነው፣ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ለሕጉ አይታዘዙም፡፡ በአዲስና በአክራሪነት ልብስ አጊጠው በሚመጡ ባልተያያዙ ንድፈ ሀሳቦች ውስጥ መጋፈጥ ያለብን ሰብዓዊ አለማወቅና ሞኝነት አለ፡፡ እነዚህ ነገሮች ንድፈ ሀሳቦች ሲሆኑ በውስጣቸው ምክንያት የሌላቸው ስለሆኑ ለመጋፈጥ የበለጠውን ከባድ ይሆናል፡፡ {2SM 98.2} Amh2SM 98.2
ጥቂት እውነት ያላቸው፣ ነገር ግን ከመጀመሪያው እውነት የሚያርቁ የውሸት ህልሞችና የውሸት ራዕዮች ይኖራሉ፡፡ ሰዎች እነርሱን ለይተው የሚያውቁበትን ደንብ ጌታ ሰጥቷቸዋል፡፡ «ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ፣ እንደዚህ ያለውን ቃል ባይናገሩ ብርሃን በውስጣቸው ስለሌለ ነው» (ኢሳ. 8፡ 20)፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ ካንቋሸሹ፣ በመንፈሱ ምስክርነቶች ለተገለጸው ለእርሱ ፈቃድ ጆሮአቸውን ካልሰጡ አሳሳቾች ናቸው፡፡ ከመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አድርገው በሚያምኑት ስሜትና ግምት ቁጥጥር ሥር ስለሆኑ ይህንን ስሜታቸውንና ግምታቸውን በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ከተጻፈው ቃል የበለጠ ተአማኒነት ያለው አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ እያንዳንዱ ሀሳብና ስሜት መንፈስ ቅዱስ ያሳደረው አሻራ ነው ብለው ይናገራሉ፤ ያለ ቅዱሳን መጻሕፍት ለመከራከር ሲሞከር የበለጠ ተአማኒነት ያለው ነገር እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ እየተመሩ እንደሆኑ እያሰቡ ቢሆኑም በእውነታው ግን ሰይጣን በውስጣቸው ያስቀመጠውን ስሜት (የአእምሮ ፈጠራ) እየተከተሉ ናቸው፡፡ --Bible Echo, September, 1886. {2SM 98.3}. Amh2SM 98.3