የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
«ምንም የሚያስጠላ ነገር” አለማየት ለተቀባይነት ትክክለኛ የሆነ መሠረት አይደለም
የአና ፊሊፕስን ጽሁፎች በተመለከተ ለመከተል የተሻለው መንገድ የትኛው እንደሆነ ግራ ልትጋቡ ትችሉ ይሆናል፡፡ ምንም ነገር በጥድፊያ መደረግ እንደሌለበት ሀሳብ እሰጣለሁ፡፡ ለዚህች እህት በጣም ርኅራኄ ይሰማኛል፡፡ እሷን ለመጉዳት ምንም ነገር አልልም አላደርግምም፡፡ ጽሁፎቹ ሳይፈተኑ ወይም ትክክለኛነታቸው ሳይረጋገጥ በታላቅ ጉጉት ስለተያዙና ስለተሰራጩ ልክ እንደ መርዝ ቆጥሮ ለመሰብሰብና ለማጥፋት የጥድፊያ እርምጃ አይወሰድ፡፡ ሀላፊነት ባላቸው በእኛ ሰዎች ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው በሄዱበት ይቆዩ፡፡ አሁን ድንገተኛ እንቅስቃሴ ማድረግ ጉዳት ያመጣል፡፡ {2SM 93.4} Amh2SM 93.4
ለእኔ ትልቅ ድንቅ የሚሆንብኝ ነገር ቢኖር ወንድሞቻችን በእነዚህ ነገሮች ውስጥ ምንም የሚያስጠላ ነገር ማየት ስላልቻሉ መቀበላቸው ነው፡፡ ለእነዚህ ጽሁፎች ማረጋገጫ ለመስጠትና ጉልበት ከሚሰጣቸው የተጽእኖ ኃይል ጋር ለመላክ የሚያስችል ባሕርይ ያለው ምን ነገር በውስጣቸው እንዳለ ለምን አልተመለከቱም? {2SM 94.1} Amh2SM 94.1
አሁን ማለት የማልፈልጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፣ ከአሁን በኋላ መናገር አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህቺን እህት ለመጉዳት ምንም ነገር ባላደርግም ዝም ለማለት አልደፍርም፡፡…ልዩ በሆነ ቦታ ተቀምጫለሁ፣ እንዲህ ባይሆን ኖሮ በዚህ ርዕስ ላይ መናገር አስፈላጊ እስከሚሆንብኝ ድረስ በዚህ መልክ አይያዝም ነበር፡፡ ማድረጉ ያሳዝነኛል፣ የወደፊቱን አደጋ ባልመለከት ኖሮ ጉዳዩን በተመለከተ አንድ ቃል እንኳን ሳልናገር እንዲያድግ ዝም እል ነበር፣ ወንድሞቼና እህቶቼም እነዚህን በፍጹም ልዩ ያልሆኑትን መገለጦች በተመለከተ የራሳቸውን መንገድ እንዲከተሉ እተዋቸው ነበር፡፡…በእህት ፊሊፕስ ጽሁፎች ውስጥ አሁን የተፈጠሩትን አይነት እንቅስቃሴዎች ሊፈጥር የሚችል ምንም ነገር ማየት አልቻልኩም፡፡ የዚህ አይነት ተፈጥሮ ያላቸው ነገሮች እንዲህ ባለ ታላቅ ጉጉት ተቀባይነት የሚያገኙ ከሆነ በአንዳንድ መልካቸው የተለያዩ ቢሆኑም ተመሳሳይ በሆነ እምነት ልትይዙአቸው የምትችሏቸውን ብዙ ነገሮች ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡ አዝናለሁ፣ በጣም አዝናለሁ፡፡ {2SM 94.2} Amh2SM 94.2
ተቀባይነት የሌላቸው ሀሳቦች በተለየ ሁኔታ የት ቦታ ላይ እንዳሉ መጠቆም እንዳለብኝ የምታስቡ ይመስለኛል፡፡ በተጻፈው ነገር ውስጥ ይህን ያህል በጣም ግልጽ የሆነ ነገር የለውም፤ ምንም የማይገባ ነገር ማግኘት አልቻላችሁም፤ ነገር ግን ይህ እነዚህን ጽሁፎች በተጠቀማችሁበት ሁኔታ እንድትጠቀሙ ሰበብ ሊሆናችሁ አይችልም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የተከተላችሁት መንገድ በማያሻማ ሁኔታ የማይገባ ነው፡፡ እንድትጠነቀቁ ለማድረግ ወዲያውኑ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ጉዳት የሚያስከትል ነገር ለይታችሁ ማወቅ አስፈላጊ ነውን? ይህን የመሰለ ነገር ካልታየ ለእነዚህ ጽሁፎች ማረጋገጫችሁን ለመስጠት በቂ ምክንያት ነውን?... {2SM 94.3} Amh2SM 94.3
የምትከተሏቸው መንገዶች በኋላ የሚያመጡትን መዘዝ በደንብ ሳታስቡበት እና ጥልቅ የሆነ መረዳት ሳይኖራችሁ የዚህ ዓይነት ተፈጥሮ ያላቸውን ጽሁፎች አታሰራጩ፡፡. . . {2SM 94.4} Amh2SM 94.4
አክራሪነት በመካከላችሁ ይታያል፡፡ ከተቻለ የተመረጡትን እንኳን ሊያስቱ የሚችሉ ማታለያዎች ይመጣሉ፡፡ በእነዚህ መገለጦች ውስጥ የሚታይ ሥርዓት አለመከተልና እውነተኛ ያልሆኑ ቃላቶች ግልጽ ከሆኑ ከታላቁ መምህር ከናፍር የሚወጡ ቃላቶች አይደሉም፡፡ ይህ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሊነሱ ከሚችሉ ብዙና የተለያዩ ዓይነት አደጋዎች የተነሳ ነው፡፡ የአደጋ ምልክትን እያንጠለጠልኩ ያለሁበት ምክንያት የእግዚአብሔር መንፈስ በሚገልጥልኝ ሁኔታ ወንድሞቼ ለይተው ማየት ያልቻሉትን ማየት ስለምችል ነው፡፡ ለእኔ ከማታለያዎች ለመጠበቅ እነዚህን ልዩ የሆኑ የማታለያ ክፍሎችን ሁሉ መጠቆም አዎንታዊ አስፈላጊነት ላይኖረው ይችላል፡፡ ለእኔ ተጠበቁ ብዬ መንገር በቂ ነው፤ እንደ ታማኝ ዘቦች ከጌታ የተሰጠ ነው የሚባለውን ነገር ሁሉ ሳይለዩ እንዳይቀበሉ የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፡፡ {2SM 95.1} Amh2SM 95.1
ስሜትን ለማነሳሳት ከሰራን የፈለግነውን ሁሉ እና መቆጣጠር ከምንችለው በላይ የሆነ ነገር እናገኛለን፡፡ በእርጋታና በግልጽ «ቃሉን ስበክ” (2ጢሞ. 4፡ 2)፡፡ የሰዎችን ስሜት ማነሳሳት ሥራችን እንደሆነ አድርገን ማየት የለብንም፡፡ ጤናማ የሆነ ስሜት መፍጠር የሚችል የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይስራ፤ ሰብአዊ ወኪል በመከታተል፣ በመጠበቅ፣ በመጸለይ እና ኢየሱስን በመመልከት፣ ብርሃንና ሕይወት በሆነው ክቡር መንፈስ በመመራትና በቁጥጥሩ ሥር በመሆን በፊቱ በቀስታ ይሂድ፡፡ {2SM 95.2} Amh2SM 95.2
በክርስቶስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ሰዎች ምልክት ይፈልጋሉ፡፡ ያኔ ምንም አይነት ምልክት እንደማይሰጣቸው ጌታ ነገራቸው፡፡ አሁንም ሆነ ሁል ጊዜ መታየት ያለበት ምልክት ቢኖር በተቻለ መጠን ቃሉን ማራኪ ለማድረግ በአስተማሪው አእምሮ የሚሰራው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሞተ፣ ደረቅ ንድፈ ሀሳብ ሳይሆን መንፈስና ሕይወት ነው፡፡ ሰይጣን የሰዎችን አእምሮ ከእግዚአብሔር ቃል ከማራቅና እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነገር ከቃሉ ውጭ እንዲፈልጉ ወይም እንዲጠብቁ ከማድረግ የበለጠ የሚፈልገው ምንም ነገር የለውም፡፡ ትኩረታቸው ወደ ሕልሞችና ራዕዮች መሳብ የለበትም፡፡ የዘላለም ሕይወት ማግኘት ካለባቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ሥጋ መብላትና ደሙን መጠጣት አለባቸው፡፡ --Letter 68, 1894. {2SM 95.3} Amh2SM 95.3