የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

66/349

በመንፈስ ምሪት የተሰጡ ምክሮችን በተመለከተ የተሳሳተ እና ትክክለኛ አጠቃቀም

[ለሚስተር ጋርማየር የተላከ.---ከአሰባሳቢዎች] Amh2SM 82.2

ወንድሜ ሆይ፣ ራስህ ተታለህ ሌሎችንም አታልለሃል፡፡ ቅዱሳን መጻሕፍትን በትክክለኛው መንገድ አልመረመርክም፡፡ እነሱን መመርመር ያለብህ የራስህን ንድፈ ሀሳብ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሳይሆን የእግዚአብሔርን አእምሮ ለመማር ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል የምታነበው በራስህ አመለካከቶች ብርሃን ነው፡፡ የውሸት ሕንጻ ትገነባና ይህን ይደግፉልኛል ብለህ በምታስባቸው ጥቅሶች ታጥረዋለህ፤ ነገር ግን ስህተትነቱን የሚያረጋግጡ ጥቅሶችን ትተህ ታልፋቸዋለህ፡፡ «የእምነቴ መሠረት መጽሐፍ ቅዱስ ነው» ትላለህ፡፡ በርግጥ ነውን? መልሱን እኔ እመልሳለሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የአንተን አቋም አይደግፍም፡፡ ደግሞ «ከመጽሐፍ ቅዱስ ስህተቴን አሳይኝና አመለካከቶቼን እተዋለሁ” ትላለህ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚላቸውን ነገሮች ከአውዱ ነጥለህ በተሳሳተ ሁኔታ እየተጠቀምክ እያለህ እንዴት ስህተትህን ልታምን ትችላለህ? ይህን በማድረግህ እግዚአብሔር ሊደርስህና ሊያሳምንህ የሚችልበትን ብቸኛ ምንጭ ታቋርጣለህ፡፡ {2SM 82.2} Amh2SM 82.3

ቅዱሳን መጻሕፍትን ለመመርመር ብቸኛው እውነተኛ መንገድ እያንዳንዱን አግባብ የሌለው ጥላቻ፣ እያንዳንዱን አስቀድሞ የተያዘ አመለካከት በምርምር በር ላይ አስቀምጠህ ዓይንህን በእግዚአብሔር ክብር ላይ በማተኮር፣ ማስተዋልን ለእምነት ክፍት በማድረግ እና ልብህ ጌታ የሚልህን ነገር ለማመን ለስልሶ ወደ ሥራ መግባት ነው፡፡ {2SM 82.3} Amh2SM 82.4

በመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም ላይ የሰዎች አመለካከቶች ብዙና የተለያዩ ናቸው፤ ነገር ግን ቅዱሳን መጻሕፍት ከሰዎች ሀሳቦች ጋር ለመግጠም አይለወጡም፡፡ የተባረከው መጽሐፍ አዎን እና አሜን ነው፤ የጸና እና ዘላለማዊ ሆኖ ይኖራል፡፡ የሰዎች ትርጓሜዎች ሁሉ አይስማሙም፣ ነገር ግን ታላቅና የተባረኩ እውነታዎች አይለወጡም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የማይለወጥ ነው፤ «ተጽፏል፡፡” {2SM 82.4} Amh2SM 82.5

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ጥቅም ከሰጣቸው ምስክርነቶች የተወሰኑ ክፍሎችን በመውሰድ የራስህን የስህተት ንድፈ ሀሳቦች ለመደገፍ፣ ምስክርነቶች የማይስማሙበትንና ሁል ጊዜ ሲነቅፉ የኖሩትን ትምህርት ለማስተማር የሰማይን ብርሃን በመዋስ ወይም በመስረቅ በስህተት ሥራ ላይ አውለሃል፡፡ ከዚህ የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስንና ምስክሮችን በስህተት ማዕቀፍ ውስጥ ታስቀምጣለህ፡፡ በስህተት ውስጥ ያሉ ሁሉ አንተ እንዳደረግከው ያደርጋሉ፡፡… በምስክርነቶች ላይ ትክክለኛ የሆነ እምነት የለህም፡፡ እምነት ቢኖርህ ኖሮ መታለልህን የጠቆሙትን ትቀበል ነበር፡፡ ከተበከሉ ምንጮች ስትጠጣ ነበርክ፡፡. . . {2SM 83.1} Amh2SM 83.1

የሆነ አዲስ፣ እንግዳና አስደናቂ የሆነ ነገር፣ በሕዝባችን ለረዥም ጊዜ እውነት ሆኖ ተይዞ ከነበረው ነገር ተቃራኒ የሆነ ነገር፣ ለዓለም ለመስጠት የሰይጣንን አስተያየቶች ለመቀበል ተዘጋጅተህ ነበር፡፡ የሴት ልጅህ የውሸት ምርቶች ትልቅ ሥራ እንድትሰራ ከፍ ከፍ አድርገውሃል፡፡ ከምትገምተው በላይ የሆኑ ውጤቶችን በማምጣት ተደልለሃል ራስህንም የጠላት ወኪል አድርገሃል፡፡ ጠላትነትን ብቻ የሚቀሰቅሱ መናፍቅነቶችንና ንድፈ ሀሳቦችን አሳትመሃል፡፡ ውጤቱ ለቤተሰብህና አንተ ያመጣሃቸውን የውሸት ንድፈ ሀሳቦች ለሚቀበሉ ሁሉ በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ወንድም ጋርማየር፣ አንተ ለራስህ ማድረግ ያለብህና ማንም ሌላ ሰው ሊያደርግልህ የማይችል ሥራ አለህ፣ ያውም ልብህን በእግዚአብሔር ፊት ትሁት ማድረግ፣ ኃጢአቶችህን መናዘዝ እና መለወጥ ነው፡፡ {2SM 83.2} Amh2SM 83.2