የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

62/349

«እኔ አልላኳቸውም”

እግዚአብሔር ሰጥቶናል የሚሉ ራዕዮችን የሚነግሩ ደብዳቤዎች ከተለያዩ ሰዎች መጥተውልኛል፣ ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ «አትመኑአቸው፣ እኔ አልላኳቸውም” ብሎ ይነግረኛል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ሲስተር ኋይት በስህተት ውስጥ እንዳለችና አንዳንድ እውነት ያልሆኑ ነገሮችን እንድታምን እና አንዳንድ እውነት የሆኑ ነገሮችን እንዳታምን መሪዎች ተጽእኖ እንዳሳደሩባት እግዚአብሔር አሳይቶናል ብለው ጽፈውልኛል፡፡ ነገር ግን በድጋሚ እንዲህ የሚል ቃል መጣልኝ፣ «አትስሚአቸው፤ እኔ አልተናገርኳቸውም፣ ምንም ዓይነት ቃል ወይም መልእክት አልሰጠኋቸውም፡፡ ሰይጣን ከሰጣቸው ሀሳቦች የውሸት ቃላትን አድርተዋል፡፡» {2SM 76.2} Amh2SM 76.2

አንዳንዶች ክርስቶስ ነን እያሉ ወደ እኔ መጥተው በግልጽ ተአምራቶችን ፈጽመዋል፡፡ ጌታ በብዙ ነገሮች እንደመራኝ ከነገሩኝ በኋላ ሰንበት የመፈተኛ ጥያቄ አለመሆኑን፣ የእግዚአብሔር ሕግ በሰዎች ላይ አስገዳጅ አለመሆኑን፣ ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር ክርስቶስን መቀበል እንደሆነ እና እነርሱ ራሳቸው ክርስቶስ እንደነበሩ ነገሩኝ፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ማስመሰሎች ጋር ልምምድ ስላለኝ በእነርሱ ላይ እምነት የለኝም፡፡ «ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ፡- እንዲህ ያለውን ቃል ባይናገሩ በውስጣቸው ብርሃን ስለሌላቸው ነው» (ኢሳ. 8፡ 28)፡፡ {2SM 76.3} Amh2SM 76.3

በአንድ ቦታ፣ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ አራት ግለሰቦች ከጌታ ጋር ግንኙነቶችን እንደፈጠሩ እየተናገሩ ስህተቶችን ይገስጹ ነበር፣ ኋላ ተፈጻሚ የሆኑ ነገሮችንም ተነበዩ፡፡ ይህ ድርጊታቸው ሰዎች በእነርሱ ላይ እምነት እንዲጥሉ አደረገ፡፡ ነገር ግን ያልተፈጸሙት ነገሮች በጨለማ ውስጥ ተደበቁ፣ ወይም ኋላ ሊስተዋሉ የሚችሉ ምስጢራዊ ነገሮች እንደሆኑ ተደርገው ተያዙ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች እነዚህን መገለጦች ከየት ነው የተቀበሉት? የተቀበሉት ብዙ ከሆኑ ሰይጣናዊ ወኪሎች ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች እንድጋፈጥና እነርሱን በመቃወም ጽኑ የሆነ ምስክርነት እንድሸከም ጌታ ሀላፊነት ሰጥቶኛል፡፡... {2SM 76.4} Amh2SM 76.4

ብዙዎች በራዕይ ሲወሰዱ አይቻለሁ፤ ነገር ግን የተቆጣጠራቸውን መንፈስ ስገስጸው ወዲያውኑ ከራዕይ ይወጡና በትልቅ የአእምሮ ሥቃይ ውስጥ ሆነው ነበር፡፡ {2SM 77.1} Amh2SM 77.1