የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

60/349

መለኮታዊ መረጃዎች

የሴት ልጅህን የውሸት ራዕዮች ጌታ ከሚሰጠኝ ራዕዮች ጋር በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ስለምታስቀምጥና በዚህ ድርጊትህ ጌታ እንድሰራው የሰጠኝን ሥራ ቅድስናውንና የከበረ ባሕርዩን ዝቅ ስለምታደርግ በምስክርነቶች ላይ ብዙ እምነት እንዳለህ መግለጽህና ማጉላትህ ለእኔም ሆነ ለሥራዬ ምንም አይጠቅምም፡፡ {2SM 74.1} Amh2SM 74.1

እግዚአብሔር በልጅህ በኣና አማካይነት ለአንተና ለሌሎች እንደነገረ አድርገህ የምትነግራቸው ነገሮች ከእሱ አለመሆኑን በግልጽ ነግሮኛል፡፡ መለኮታዊ ማረጋገጫ የላቸውም፡፡ ልጅቷን የሚቆጣጠረው ሌላ መንፈስ ነው፡፡ በእሷ ውስጥ እየሰራ ያለው ጠላት ነው፡፡ በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የዚህ ዓይነት መገለጦች እጅግ የተለመዱ እየሆኑ ይሄዳሉ፡፡ ወደ አንድነትና ወደ እውነት ሁሉ አይመሩም፣ ነገር ግን ከእውነት ያርቃሉ፡፡ {2SM 74.2} Amh2SM 74.2

እነዚህ እንቅስቃሴዎች ከእግዚአብሔር ላለመሆናቸው ያለን አንድ ጽኑ የሆነ ማስረጃ ስህተት መሆናቸውን ከምናውቃቸው ከአንተ አመለካከቶች ጋር የሚስማሙ መሆናቸው ነው፡፡ በራዕይ እንደምታያቸው የምትናገራቸው ነገሮች በእግዚአብሔር ቃል የተደገፉ አይደሉም፣ ነገር ግን የቃሉ ተቃራኒ ናቸው፡፡ በእሷ አማካይነት፣ በጽድቅ ካባ ስር፣ ተራነትን፣ መናፍቅነትን እና እርኩሰትን ለማምጣት ሰይጣን በራሱ መንፈስ ሊሞላት ያለማቋረጥ ሥራ ላይ ነው፡፡ የእሷን ንግግሮች ከእግዚአብሔር እንደሆኑ አድርገህ እስከቆጠርክ ድረስ በእውነተኞቹ ምስክርነቶች ላይ ያለህ እምነት ዋጋ ቢስ ነው፤ በመሆኑም አንተና በአንተ ሀሳቦች ላይ እምነት ያላቸው ሁሉ ውሸትን ለማመን አልፋችሁ እንድትሰጡ ሰይጣን እግዚአብሔር ካዘዛቸው ወኪሎች ጋር ግንኙነት እንዳይኖራችሁ ለማድረግ ተስፋ ያደርጋል፡፡ ቅዱሳን መጻሕፍት ስለተታለሉትና እየተታለሉ ስላሉት ይናገራሉ፡፡ ይህ አንተ ያለህበት ሁኔታ ነው፡፡ አንተ ልጅህን ታስታለህ፤ እሷ አንተን ታስታለች፣ እውር እውርን እየመራ ነው፡፡ ጠላት በፈተናዎች አማካይነት ሊያታልላቸው እንደሚችል ከሚያስባቸው ሰዎች ሁኔታዎች ጋር በደንብ ይገጥማሉ ብሎ በሚመለከታቸው በተለያዩ መንገዶች ዓላማዎቹን ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ {2SM 74.3} Amh2SM 74.3

የሴት ልጅህ የኣና መልእክቶች ከእግዚአብሔር አለመሆናቸውን በግልጽ እነግርሃለሁ፡፡ ይህን ጌታ አሳይቶኛል፣ እሱ ደግሞ አይዋሽም፡፡ ብዙ ጥሩ ነገሮችን ልትናገር ትችላለች፣ እውነት የሆነ ብዙ ነገር ልትናገር ትችላለች፣ ነገር ግን የነፍሳት ጠላትም ይህን ያደርጋል፡፡ አስመሳይ የሆነው በብዙ መንገድ እውነት ይመስላል፡፡ ባሕርይን የሚገልጸው የሚፈራው ፍሬ ነው፡፡... {2SM 74.4} Amh2SM 74.4