የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

54/349

ቤተ ክርስቲያን አትፈረካከስም

እንደገና እላለሁ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የምትጠብቀውን ቤተ ክርስቲያን ባቢሎን ብሎ በሚጠራ በማንኛውም መልእክተኛ አማካይነት እግዚአብሔር አልተናገረም፡፡ እንክርዳዶች ከስንዴ ጋር መኖራቸው እውነት ነው፤ ነገር ግን መጀመሪያ እንክርዳዱን በእሳት እንዲቃጠል ሰብስበው እንዲከምሩ መላእክቱን እንደሚልክ ጌታ ተናግሯል፣ ስንዴውን ግን ወደ ጎተራ ይሰበስባል፡፡ ጌታ ቤተ ክርስቲያኑን እንደሚወድ አውቃለሁ፡፡ ቅንጅት እንድታጣና እርስ በርሳቸው ግንኙነት ወደሌላቸው ጥቃቅን አቶሞች እንድትከፋፈል አይፈልግም፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አነስተኛ የሆነ ስምምነት እንኳን የለም፤ እንደዚህ ዓይነት ነገር እንደሚሆን የሚደግፍ አነስተኛ የሆነ ማስረጃ እንኳን የለም፡፡ ይህን የሀሰት መልእክት የሚሰሙና ሌሎችንም ሊያበላሹ የሚሞክሩ ይታለሉና ከዚያ የበለጠ ማታለያ ለመቀበል በመዘጋጀት ወደ ባዶነት ይመጣሉ፡፡ {2SM 68.3} Amh2SM 68.3

ምንም እንኳን ለላውዶቂያ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠው መልእክት ለእነርሱ የሚሆን ለመሆኑ ማስረጃዎች በማስረጃዎች ላይ ቢከመሩም በአንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባላት መካከል ኩራት፣ በራስ ብቃት መታመን፣ በትዕቢት የተሞላ አለማመን እና የራሳቸውን ሀሳቦች ለመተው ፈቃደኛ አለመሆን አለ፡፡ ነገር ግን ያ ቤተ ክርስቲያን እንዳትኖር አይፍቃትም፡፡ ስንዴውና እንክርዳዱ እስከ መከር ድረስ አብረው እንዲያድጉ ተውአቸው፡፡ ያኔ የመለየቱን ሥራ የሚሰሩት መላእክት ናቸው፡፡ {2SM 69.1} Amh2SM 69.1

እያንዳንዱን አዲስ ሀሳብ እና ትልቅ ብርሃን አለን የሚሉትን በምትቀበሉበት ሁኔታ እንድትጠነቀቁ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶችን አስጠነቅቃለሁ፡፡ የስራቸው ባሕርይ የመክሰስና የመለያየት ይመስላል፡፡ {2SM 69.2} Amh2SM 69.2

ወንድሜ ሆይ፣ ተጠንቀቅ እልሃለሁ፡፡ አሁን በገባህበት መንገድ አንድ እርምጃ እንኳን አትሂድ፡፡ «ጨለማ እንዳይመጣብህ ብርሃን እያለልህ” በብርሃን ሂድ (ዮሐ. 12፡ 35)፡፡ {2SM 69.3} Amh2SM 69.3

በባትል ክሪክ ቀዝቀዝ ባለ ሁኔታ እንደተያዝህ ብሶትህን ትናገራለህ፡፡ መንፈሳዊ ወደ ሆኑ ሰዎች በትሁት መንፈስ ሄደህ «ከእኔ ጋር ቅዱሳን መጻሕፍትን ትመረምራላችሁን? በዚህ ጉዳይ ላይ አብረን መጸለይ እንችላለንን? እኔ ብርሃን የለኝም፣ እፈልገዋለሁ፤ ስህተት ነፍስን በፍጹም አይቀድስም» ብለሃቸዋልን? ካለፉበት ልምምድ በኋላ እምነት ሊጥሉብኝ ይገባል ብለህ ያሰብከውን ያህል ስላልተማመኑብህ ትገረማለህን? የክርስቶስ ቃላት ምንም ክብደት አይኖራቸውምን? «የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኩላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ” (ማቴ. 7፡ 15)፡፡ «እነሆ ክርስቶስ እዚህና እዚያ ነው» ማለት ይበዛል፡፡ አማኞች «አብራችሁ ግፉ» ያለውን የመልአኩን ድምጽ ይስሙ፡፡ ጥንካሬያችሁ በአንድነታችሁ ውስጥ ነው፡፡ በወንድማማች መዋደድ ተዋደዱ፣ ርህሩሆችና ትሁታን ሁኑ፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አለችው፣ ስለዚህች ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስ እንዲህ ብሏል፣ «የገሃነም ደጆች አያሸንፉአትም» (ማቴ. 16፡ 18)፡፡ ጌታ የሚልካቸው መልእክተኞች መለኮታዊ የሹመት ደብዳቤ አላቸው፡፡ ለአንተ የገርነት ስሜት አለኝ፣ ነገር ግን ወደ ብርሃን እንድትመጣ እማጸንሃለሁ፡፡ --Letter 16, 1893. {2SM 69.4} Amh2SM 69.4