የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ምዕራፍ 1—ስሜትን የሚያነሳሱ ትምህርቶችንና ስሜታዊ ኃይማኖትን በተመለከተ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች
በግምት የተፈጠሩ ሀሳቦች የሚያስከትሉት አደጋ
ወደ እግዚአብሔር ሕዝብ እየመጣ ያለ የመከራ ጊዜ አለ፣ ነገር ግን ይህንን ሁል ጊዜ በሕዝብ ፊት ማቅረብና የመከራ ጊዜ አስቀድሞ እንዲያገኛቸው ማድረግ የለብንም፡፡ በእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል ብጠራ ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ ወደ ቤተ ክርስቲያናት መወሰድ ያለበት የወቅቱ እውነት አይደለም፡፡ ብጠራ የቀረበውን እውነት ለመቀበል ፈቃደኛ ያለመሆን ውጤት ይሆናል፡፡ {2SM 13.1} Amh2SM 13.1
አገልጋዮች አስደናቂ የሆኑ ከፍተኛ ሀሳቦች እንዳሏቸው ሊሰማቸው አይገባም፣ ሁሉም ይህን ሀሳብ ካልተቀበሉ ይበጠሩና በእነርሱ ፋንታ ለድል ወደ ፊትና ወደ ላይ የሚሄድ ሕዝብ ይነሳል፡፡ ሰዎች በላውዶቂያነት ሁኔታ፣ ለብ ብለው፣ ሐብታምና እጅግ የሞላላቸው እንደሆኑና ምንም እንደማያስፈልጋቸው ሲሰማቸው እንደሚሆን ሁሉ ከክርስቶስ ቀድመው በመሮጥ እርሱ በእጃቸው ኃላፊነት ያልሰጣቸውን ሥራ ሲሰሩ የሰይጣን ዓላማ ይፈጸማል፡፡ በሁለቱም ክፍል ያሉ ሰዎች በእኩል ደረጃ የመሰናከያ አለቶች ናቸው፡፡ {2SM 13.2} Amh2SM 13.2
አዲስ ሀሳብን ለማምጣት እያቀዱ ያሉና ያላቸውን እያንዳንዱን ኃይል እየተጠቀሙ ያሉ አንዳንድ ቀናኢ የሆኑ ሰዎች የሆነ አስገራሚ፣ አስደናቂ፣ መሳጭ፣ እና ሌሎች ሊገነዘቡት የማይችሉትን ነገር ለማግኘት ጥረት በማድረግ አሰቃቂ ስህተት ፈጽመዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ስለ ምን እየተናገሩ እንደሆነ እነሱ ራሳቸው አያውቁም፡፡ ለራሳቸውም ሆነ ለቤተ ክርስቲያናት የሚጠቅም ቅንጣት ነገር የሌላቸውን ሀሳቦች በማስፋፋት በእግዚአብሔር ቃል ላይ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ፡፡ ለጊዜው ስሜትን ሊያነሳሱ ይችላሉ፤ ነገር ግን እነዚህ ሀሳቦች አጸፋ ስላላቸው ራሳቸው እንቅፋት ይሆናሉ፡፡ እምነት ለፈጠራ አልፎ ስለተሰጠ አመለካከቶቻቸው አእምሮ ወደ ስህተት አቅጣጫ እንዲያደላ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያሉ ግልጽና ቀላል የሆኑ ዓረፍተ ነገሮች ለአእምሮ ምግብ እንዲሆኑ ፍቀዱላቸው፡፡ በቃሉ ውስጥ በግልጽ ባልተሰጡ ሀሳቦች ላይ ማሰላሰል አደገኛ የሆነ ነገር ነው፡፡ --Manuscript 82,1894. {2SM 13.3} Amh2SM 13.3
ወደ ፊት ቤተ ክርስቲያኖቻችንን የሚያሰጋው አደጋ ቢኖር የሰዎችን አእምሮ ግራ የሚያጋቡ አዳዲስና እንግዳ የሆኑ ነገሮች ወደ ቤተክርስቲያን መምጣታቸውና በመንፈሳዊ ነገሮች ጥንካሬ እጅግ በሚያስፈልጋቸው ሰዓት ምንም ዓይነት ጥንካሬ አለመኖር ነው፡፡ አዳዲስና እንግዳ የሆኑ ነገሮች በዚህ ወቅት መሰጠት ያለበት መልእክት አካል በመሆን ከእውነት ጎን ለጎን እንዳይቀመጡ በግልጽ ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለዓለም ስንሰጥ የነበረው መልእክት ጎልቶ እንዲታይ መደረግ አለበት፡፡ --An Appeal for Canvassers, pp. 1, 2. {2SM 14.1} Amh2SM 14.1