የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

48/349

ክፍል 2—የተሳሳቱ እና አስነዋሪ እንቅስቃሴዎች

መግቢያ

በአመታት ውስጥ በርካታ የስህተት ወይም ኃይማኖትን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎች፣ ለመጽሐፍ ቅዱስ በሚሰጥ የስህተት ትርጉም ላይ ወይም መለኮታዊ ብርሃን ነው ተብሎ በሚታሰብ ነገር ላይ በመመስረት፣ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች መካከል ተነስተዋል፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች በተነሱ ጊዜ ሁኔታዎቹን ለመጋፈጥ በትንቢት መንፈስ በተሰጡ ምክሮች ውስጥ በጽናትና በሀቀኝነት መፍትሄ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ከእነዚህ ምክሮች አንዳንዶቹ በዚህ ክፍል ውስጥ ተካትተዋል፡፡ {2SM 62.1} Amh2SM 62.1

በተለምዶ አዲስ ብርሃን ነው ተብሎ ከሚታሰብ ነገር ጋር ግንኙነት የነበረው ቤተ ክርስቲያንን እና መሪዎቿን የመኮነን መልእክት፣ እና ጊዜ የመወሰን ክፍል ነበረው፡፡ በኤ ኤም አር ስታንተን የተመራ የሶስተኛው መልአክ ታላቅ ጩኸት ተብሎ ስም የተሰጠው አንድ የዚህ ዓይነት እንቅስቃሴ በ1893 ዓ.ም ሪቪው ኤንድ ሄራልድ በሚለው መጽሔት ላይ «ቅሬታዋ ቤተ ክርስቲያን ባቢሎን አይደለችም» በሚል ርዕስ በተጻፉ ጽሁፎች ተተችቷል (ጽሁፎቹ አሁን ቴስቲሞኒስ ቱ ሚኒስተርስ በሚል መጽሐፍ ገጽ 32-36፣ እና ዘ ሬምነንት ቸርች በሚል መጽሐፍ ገጽ 23-53 ላይ ይገኛል)፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የተሰባሰቡ ነገሮች ለዚህ እንቅስቃሴ ተጨማሪ መግለጫ በመሆን በርካታ ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎችን በጥልቀት ይዳስሳሉ፡፡ {2SM 62.2} Amh2SM 62.2

የትንቢት ስጦታ እንዳላቸው የሚናገሩ ሁለት ታዋቂ ጉዳዮች ደግሞ ሚስስ ኋይት በጉዳዩ ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለተሳተፉ ሰዎች በምክር መልክ በሰጠቻቸው ነገሮች ውስጥ ቀርቧል፡፡ የዚህ አይነት ባሕርይ ያላቸውን ሁኔታዎች ስታወሳ እጅግ በጣም በቋፍ ላይ ሆና ነበር፣ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልእክተኛ፣ ተግባሯን በመፈጸም ረገድ፣ ትንቢታዊ ሥራን በተመለከተ ከሚያስመስሉ ከእነዚህ አስመሳዮች ቤተ ክርስቲያንን የተከላከለ መመሪያ ተሰጥቷት ነበር፡፡ ትክክለኛ የሆነ የትንቢት ስጦታ ግልጽና አሳማኝ በሆኑ ብዙ ማስረጃዎች በመታጀብ የራሱን መረጃዎች እንደሚይዝ አጽንዖት ሰጥታለች፡፡ {2SM 62.3} Amh2SM 62.3

የእውነት ጠላት እስካለ ድረስ እምነትን የሚቃወሙና የስህተት እንቅስቃሴዎች ስለሚነሱ መጋፈጥ የግድ ያስፈልጋል፡፡ ኤለን ጂ ኋይት ከእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በርካታዎቹን ከሚያስተምሯቸው ልዩ ትምህርቶቻቸው ጋር ማሳየቷ እና ሥራቸውንና አስተምህሮአቸውን መተንተንን በተመለከተ የተሰጠው ምክር በቀላሉና በግልጽ ለመለየት እና የዚህ አይነት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ለመጋፈጥ ትልቅ ጥቅም ይሰጣሉ፡፡ --{2SM 62.4} Amh2SM 62.4

White Trustees.