የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

45/349

ውጫዊ የባሕርይ ለውጥ

ግለሰቦች በእውነት ንድፈ ሀሳቦች ረክተው በልባቸው ግን በውጫዊ ባሕርይ ለውጥ የሚገለጸው የእግዚአብሔር መንፈስ ስራ ከጎደላቸው በጌታ ሥራ ውስጥ ለበለጠ ብቃት ብቁ ከሚያደርጋቸው ችሎታ ራሳቸውን እየለዩ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሌላቸው ሰዎች ምን መስራት እንዳለባቸው ስለማያውቁና ትክክለኛውን የመለከት ድምጽ ስለማያሰሙ በጽዮን ግንብ ላይ ታማኝ ጠባቂዎች መሆን አይችሉም፡፡ {2SM 56.2} Amh2SM 56.2

በጴንጤቆስጤ ቀን የነበረው ዓይነት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ወደ እውነተኛ ኃይማኖት መነቃቃትና ብዙ አስደናቂ ሥራዎችን ወደ መስራት ይመራል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በጴንጤቆስጤ ቀንና ከዚያም በኋላ እንደሰራው ዛሬ በሰዎች ላይ ቢሰራ ኖሮ አሁን እውነትን እናምናለን የሚሉት ብዙ ሰዎች ስለ መንፈስ ቅዱስ አሰራር እጅግ ጥቂት ብቻ ስለሚያውቁ «ከወግ አጥባቂነት ተጠንቀቁ” ብለው ይጮሁ ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የተሞሉ ሰዎችን «እነዚህ ሰዎች በወይን ጠጅ ሰክረዋል” ይላሉ፡፡ {2SM 57.1} Amh2SM 57.1

ሰዎች የራሳቸውን ፈቃድና መንገድ ካልተዉና ለእግዚአብሔር ፈቃድና መንገድ ራሳቸውን አሳልፈው ካልሰጡ በስተቀር ከዚህ በፊት ከነበራቸው ወይም ወደ ፊት ሊኖራቸው ከሚችላው የበለጠ ከክርስቶስ ጋር እጅግ የቀረበ አንድነት፣ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እጅግ የቀረበ ግንኙነት የሚጎድላቸው ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ታላቁ ኃጢአት መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ልባቸውን አለመክፈታቸው ነው፡፡ ነፍሳት ክርስቶስን ሲናፍቁ እና ከእርሱ ጋር አንድ ለመሆን ሲሹ በአምልኮ መልክ የረኩ ሰዎች «ተጠንቀቁ፣ ጽንፈኞች አትሁኑ» ብለው በቃለ አጋኖ ይናገራሉ፡፡ የሰማይ መላእክት በመካከላችን ሲሆኑና በሰብዓዊ ወኪሎች አማካይነት ሲሰሩ ከጴንጤቆስጤ ቀን በኋላ የነበረው ዓይነት ጽኑ የሆነ ትልቅ ለውጥ ይኖራል፡፡ {2SM 57.2} Amh2SM 57.2

አሁንም ወንድሞች ሆይ፣ ተጠንቀቁ፣ በሰብዓዊ መነሳሳት ውስጥ አትግቡ ወይም መነሳሳትን ለመፍጠር አትሞክሩ፡፡ ነገር ግን በሰብዓዊ መነሳሳት ውስጥ እንዳንገባ እየተጠነቀቅን ሳለን የመንፈስ ቅዱስ ሥራን በተመለከተ ጥያቄ ከሚያነሱት ወይም ጥርጣሬን ከሚያስተናግዱት መካከል መሆን የለብንም፡፡ ልባቸው ስላልተነካ፣ ነገር ግን ቀዝቃዛና ሊነካ የማይችል ከመሆኑ የተነሳ የእግዚአብሔር መንፈስ ወንዶችንና ሴቶችን ስለተቆጣጠራቸው ጥያቄ የሚያነሱና የሚነቅፉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡ --Letter 27, 1894, {2SM 57.3} Amh2SM 57.3