የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ተአምራቶች በመዝጊያው ጦርነት ውስጥ
በምድር ላይ በሕይወት የሚኖሩ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በተመለከተ ያለፈው ዋይታና ሰማያዊ ክብር የሚዋሃዱበትን ልምምድ የሚገልጽ ምንም ሀሳብ መስጠት አይቻልም፡፡ ከእግዚአብሔር ዙፋን በሚወጣ ብርሃን ይሄዳሉ፡፡ በመላእክት አማካይነት በሰማይና በምድር መካከል የማይቋረጥ ግንኙነት ይኖራል፡፡ ሰይጣንም በክፉ መላእክት ታጅቦ፣ እግዚአብሔር ነኝ እያለ፣ ከተቻለው የተመረጡትን እንኳን ለማሳት ሁሉንም ዓይነት ተአምራቶች ይሰራል፡፡ ሰይጣን ሊሰራ የሚችለውን ማንኛውንም ዓይነት ተአምራት አስመስሎ ስለሚሰራ የእግዚአብሔር ሕዝብ ተአምራትን በመሥራት ከአደጋ ነጻ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ የተፈተኑ የእግዚአብሔር ሕዝብ ኃይል የሚያገኙት በዘጸአት 31፡ 12-18 ውስጥ በተነገረው ምልክት ነው፡፡ «ተጽፏል” በሚለው ሕያው ቃል አቋም መያዝ አለባቸው፡፡ ከአደጋ ነጻ ሆነው መቆም የሚችሉበት ብቸኛው መሠረት ይህ ብቻ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ቃል ኪዳን ያፈረሱ ሰዎች በዚያን ቀን በዓለም ውስጥ ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር ይሆናሉ፡፡ {2SM 54.5} Amh2SM 54.5
አራተኛው ትዕዛዝ የእርሱ የመፍጠር ኃይል ምልክትና ከሰው አክብሮትንና ስግደትን እንደሚፈልግ የሚገልጽ ምስክር ስለሆነ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ሰዎች በተለየ ሁኔታ ተለይተው የሚታወቁት ለአራተኛው ትዕዛዝ ባላቸው አክብሮት ነው፡፡ ኃጢአተኞች ተለይተው የሚታወቁት የፈጣሪን መታሰቢያ ለማፍረስና የሮምን ተቋም ከፍ ከፍ ለማድረግ በሚያደርጉአቸው ጥረቶች ነው፡፡ በግጥሚያው ላይ የክርስትናው ዓለም በሁለት ታላላቅ ክፍሎች ይከፈላል፡፡ እነርሱም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛትና የኢየሱስን ኃይማኖት የሚጠብቁ እና ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱና ምልክቱን የሚቀበሉ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን «ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም» (ራዕይ 13፡ 16) የአውሬውን ምልክትን እንዲቀበሉ ለማስገደድ ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት ኃይላቸውን አንድ ቢያደርጉም፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ አይቀበሉትም፡፡ የጳጥሞሱ ነቢይ «በአውሬውና በምስሉም በምልክቱና በስሙም ቁጥር ላይ ድል ነስተው የነበሩት የእግዚአብሔርን በገና ይዘው በብርጭቆ ባሕር ላይ ቆመው” (ራዕይ 15፡ 2) የሙሴንና የበጉን መዝሙር ሲዘምሩ ተመለከታቸው፡፡ {2SM 55.1} Amh2SM 55.1
የእግዚአብሔርን ሕዝብ አስፈሪ የሆኑ ፈተናዎች ይጠብቁአቸዋል፡፡ የጦርነት መንፈስ ነገስታትን ከአንድ የምድር ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ እያንቀሳቀሳቸው ነው፡፡ ነገር ግን እየመጣ ባለው የመከራ ጊዜ ማለትም ሕዝብ ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ዓይነት መከራ ሆኖ የማያውቅ የመከራ ጊዜ መካከል የእግዚአብሔር ሕዝብ ሳይናወጥ ይቆማል፡፡ በብርታት ከእነርሱ የሚበልጡ መላእክት ስለሚጠብቁአቸው ሰይጣንና መላእክቶቹ ሊያጠፉአቸው አይችሉም፡፡ --Letter 119, 1904. {2SM 55.2} Amh2SM 55.2