የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

347/349

አድልዎ የሌለው ፍቅር አግባብነት የሌለውን ጥላቻ ያቀልጣል

እውነተኛ የሆነ ሚስዮናዊ መንፈስ ወደ ሰዎች ልብ ሲገባ የወገንተኝነት፣ የመደብና የዘር ግድግዳዎች ይወድቃሉ፡፡ አግባብነት የሌለው ጥላቻ በእግዚአብሔር ፍቅር ይቀልጣል፡፡--Review and Herald, Jan. 21, 1896; The Southern Work, 1966 ed., p. 55. Amh2SM 486.5

በጥቁሮችና በነጮች መካከል የመለያ ግምብ ተገንብቷል፡፡ ክርስቲያኖች ለፈጣሪያቸው ከሁሉ የበለጠ ፍቅር እና ለጓረቤቶቻቸው አድልዎ የሌለበት ፍቅር እንዲኖራቸው የሚመክረውን የእግዚአብሔርን ቃል ሲታዘዙ እነዚህ አግባብነት የሌላቸው የጥላቻ ግድግዳዎች እንደ ኢያሪኮ ግንብ በራሳቸው ይፈራርሳሉ፡፡ --Review and Herald, Dec. 17, 1895; Republished in The Southern Work, 1966 ed., p. 43. Amh2SM 486.6

መንፈስ ቅዱስ ሲፈስ ሰዎች የሰብዓዊ ፍጡራንን ነፍስ መዳን ስለሚሹ ሰብአዊነት አግባብነት በሌለው ጥላቻ ላይ ድልን ይቀዳጃል፡፡ እግዚአብሔር አእምሮዎችን ይቆጣጠራል፡፡ ሰብዓዊ ልቦች ክርስቶስ እንደወደደ ይወዳሉ፡፡ የቆዳ ቀለም መለያዎች አሁን ብዙዎች ከሚመለከቱት በተለየ ሁኔታ ይታያል፡፡ ክርስቶስ እንደወደደ መውደድ አእምሮን ንጹህና ሰማያዊ በማድረግ ራስ ወዳድነት ወደ ሌለው ከባቢ አየር ከፍ ያደርጋል፡፡ --Testimonies, vol. 9, p. 209. Amh2SM 487.1