የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

38/349

ተአምራቶች መፈተኛ አይደሉም

ዛሬ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ የሚሰማሩ ሰዎች ጳውሎስ በሥራው ውስጥ የገጠሙትን ዓይነት ፈተናዎች ይጋፈጣሉ፡፡ ተመሳሳይ በሆነ የኩራትና የማታለያ ሥራው ሰይጣን የተለወጡ ሰዎችን ከእምነት ለማሳት ይፈልጋል፡፡ ልናስተናግዳቸው የማይገቡ ንድፈ ሀሳቦች ይመጣሉ፡፡ ሰይጣን ብልህ ሰራተኛ ስለሆነ አእምሮን ለማጨለምና ግራ ለማጋባት እና የድነት አስተምህሮዎችን ከሥራቸው ለመንቀል ብልጠት ያለባቸውን የስህተት ሀሳቦች ያመጣል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚነበበው አድርገው የማይቀበሉ ሰዎች በእሱ ወጥመድ ይጠመዳሉ፡፡ {2SM 52.2} Amh2SM 52.2

ዛሬ እውነትን በቅዱስ ድፍረት መናገር ያስፈልጋል፡፡ በጌታ አገልጋይ ለቀድሞዋ ቤተ ክርስቲያን የተወሰደውን ምስክርነት በዚህ ጊዜ ሕዝቡ መስማት አለባቸው፡፡ «ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን” (ገላ. 1፡ 8)፡፡ {2SM 52.3} Amh2SM 52.3

የተአምራት ሥራን የእምነቱ መፈተኛ የሚያደርግ ሰው ሰይጣን፣ በተለያዩ የማታለያ ዓይነቶች፣ እውነተኛ የሚመስሉ ተአምራቶችን መስራት እንደሚችል ያገኛል፡፡ እስራኤላውን ከግብፅ ነጻ በወጡ ጊዜ የመፈተኛ ጥያቄ ለማድረግ ተስፋ አድርጎ የነበረው ይህንን ነበር፡፡ --Manuscript 43, 1907. {2SM 52.4} Amh2SM 52.4