የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

35/349

ተአምራት ሰሪው የእግዚአብሔርን ሕግ አልቀበልም ሲል

ሰዎች በሚሉት ነገር መታመን የለብንም፡፡ ክርስቶስ እንደገለጸው በሽተኞችን በመፈወስ ተአምራት እንደሚሰሩ ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ ከኋላቸው ገና በሰዎች ፊት ከሰማይ እሳት እስከሚያወርድ ድረስ ተአምራት የሚሰራው ታላቁ አታላይ ቆሞ ሳለ ይህ አስደናቂ ነገር ሊሆን ይችላል ወይ? {2SM 49.3} Amh2SM 49.3

በግምቶችም መታመን የለብንም፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በእግሩ እየረገጠ ሳለ የእግዚአብሔርን ቃል የመታዘዝ ግዴታ የለብህም፣ ቅዱስና ኃጢአት የለሽ ነህ የሚል ድምፅ ወይም መንፈስ የኢየሱስ ድምፅ አይደለም፡፡ እሱ እንዲህ ብሏል፡- «የአባቴን ትዕዛዛት ጠብቄያለሁ» (ዮሐ. 15፡10)፡፡ ዮሐንስም እንዲህ በማለት ይመሰክራል፡- «አውቄዋለሁ የሚል ትዕዛዛቱንም የማይጠብቅ ውሸተኛ ነው እውነትም በእርሱ ውስጥ የለም” (1ዮሐ. 2፡ 4)፡፡ {2SM 49.4} Amh2SM 49.4

እነዚህ ታላቅ ኃይል ያላቸው መገለጦች እና አስደናቂ ግምቶች ዓለምን በሙሉ ለማሳት እና በውሸት እንዲያምኑ ለማድረግ ጠንካራ በሆነ ማታለያ ሰዎችን በማረከው ተአምራት ሰሪ መንፈስ ተጽእኖ በተሰጡት ላይ ተመስርቶ ካልሆነ በስተቀር እንዴት መልስ ሊሰጥባቸው ይችላል? ወንዶችና ሴቶች ታላቅ መንፈሳዊ ኃይል እንዳላቸው እየተናገሩ የእግዚአብሔርን ሕግ ችላ ሲሉ፣ በእነርሱ ባለመታዘዝ ሌሎችን ወደ ስህተት ስለሚመሩና ሰይጣን እነርሱን በሥራው ውስጥ የተዋጣላቸው ወኪሎቹ አድርጎ ሊጠቀምባቸው ስለሚችል ደስ ይለዋል፡፡ --The Signs of the Times, July 21, 1887. {2SM 49.5} Amh2SM 49.5