የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
መግቢያ
«በሽታና መንስኤው” የሚል ርዕስ የተሰጣቸው ስድስቱ ጽሁፎች ኤለን ኋይት በጤና ጉዳይ ላይ በጻፈችው ትልቅ ስብስብ ውስጥ ካሉት ቀደምት ማገናኛዎች መካከል አንዱን ይመሰርታሉ፡፡ ዳራቸው የሚከተለው ነው፡- በመጀመሪያ፣ በሰኔ 6 ቀን 1863 ዓ.ም የተቀበለችው ታሪካዊ የሆነ የጤና ተሃድሶ ራዕይ ነበር፡፡ ቀጥሎ፣ ሚስስ ኋይት በ1864 ዓ.ም መንፈሳዊ ስጦታዎች በሚለው አራተኛው መጽሐፏ ውስጥ (አሁን በትክክለኛ ቅጂ እንደገና ታትሞ ያለ) በዚህ ጉዳይ ላይ «ጤና” በሚል ርዕስ 30 ገጽ የነበረውን የመጀመሪያዋን የጽሁፍ መልእክት አቀረበች፡፡ ከዚያም በ1865 ዓ.ም ከተለያዩ ጸሐፊዎች ሥራ ተሰባስቦ ጤና ወይም እንዴት መኖር እንዳለብን በሚል ርዕስ ታትመው ለነበሩት ተከታታይነት ለነበራቸው ስድስት መጽሔቶች ለእያንዳንዳቸው ጽሁፍ አዘጋጀች፡፡ ስድስቱ የኤለን ኋይት ጽሁፎች አስቀድሞ በነበረው ዓመት መንፈሳዊ ሥጦታዎች በሚል መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን 30 ገጽ የነበረውን ጽሁፍ የሚያጎሉ ነበሩ፡፡ ኤለን ኋይት እንዴት መኖር እንዳለብን ለምትለው መጽሔት ከዚህ ሌላ ምንም አስተዋጽዖ አላደረገችም ነበር፡፡ Amh2SM 410.1
ከጤና ጋር የተገናኙና በኤለን ኋይት የተጻፉ ቀደምት መግለጫዎችን ታሪካዊ ፋይል ለመጨረስ በዚህ ቦታ የእሷ ጽሁፎች በትክክለኛ ቅጂ ይታያሉ፡፡ ቃል በቃል፣ ዓረፍተ ነገር በዓረፍተ ነገር በመባዛታቸው ምክንያት ከመቶ ዓመታት በፊት በማይመቹ ሁኔታዎች የገቡ አንዳንድ የሰዋሰው ጉድለቶችን ይይዛሉ፡፡ Amh2SM 410.2
ምንም እንኳን እነዚህ ጽሁፎች እንደገና እንዲባዙ ኤለን ኋይት ባትጠይቅም በ1899 እና በ1900 ዓ.ም በአጭር ጊዜ ተከታታይ ሕትመት በሪቪው ኤንድ ሄራልድ እንደገና ታትሞ ነበር፡፡ የኋለኛው፣ ኤለን ኋይት በጤና ርዕስ ላይ ያቀረበቻቸውን የተሟሉ ነገሮች የያዘውና በ1905 ዓ.ም የፈውስ አገልግሎት በሚል መጽሐፏ ቁንጮ ላይ የደረሰው፣ «በሽታና መንስኤዎቹ» የሚለውን ጨምሮ የብዙዎቹን ቀደምት ጽሁፎች ቦታ ወሰደ፡፡ Amh2SM 410.3
እነዚህ ጽሁፎች በተዘጋጁበት ወቅት በሕክምና ልምምድ መስክ የነበሩ ሁኔታዎችን አንባቢው ማሰብ አለበት፡፡ በተለይም የመጨረሻው ጽሁፍ መነበብ ያለበት በሚጻፍበት ጊዜ የነበረውን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች ክለሳ ለማድረግ የጤና መልእክታችን ታሪክ (ዘ ስቶሪ ኦቭ አወር ሄልዝ መሰጅ) ከሚለው መጽሐፍ የ1955 ዓ.ም እትም ገጽ 112-130፣ 166-169፣ 427-431ን፤ ኤለን ጂ ኋይት ኤንድ ሄር ክሪትክስ ከሚለው መጽሐፍ ገጽ 136-160ን፤ ቢሊቭ ሂዝ ፕሮፌትስ ከሚለው መጽሐፍ ገጽ 253-267 ን ይመልከቱ፡፡ Amh2SM 410.4
የኋይት ባለአደራዎች፡፡