የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
በሀሰት ቅድስና መማረክ
ብርሃንና እውነት የተሰጣቸው አንዳንድ ሰዎች እንዴት በፍጥነት የሰይጣንን ማታለያዎች እንደሚቀበሉና በሀሰት ቅድስና እንደሚማረኩ በማየቴ ነፍሴ እጅግ አዝናለች፡፡ በትንቢት እንደተገለጸው የቆምንበትን ማወቅ እንድንችል ጌታ ካስቀመጣቸው ምልክቶች ሰዎች ዘወር ሲሉ የት እንደሚሄዱ ሳያውቁ እየሄዱ ናቸው፡፡ Amh2SM 393.1
ከልብ የመነጨ አመጽ ሊፈወስ ይችላል ወይ? የሚል ጥያቄ ያድርብኛል፡፡ አበውና ነቢያት በሚለው መጽሐፍ ውስጥ የቆሬን፣ የዳታንን እና የአብራምን አመጽ አጥኑ፡፡ ይህ አመጽ በመስፋፋት ከሁለት ሰዎች በላይ አካትቷል፡፡ አመጹ የተመራው ታዋቂ በሆኑና የእሥራኤል ጉባኤ አለቆች በሆኑት ሁለት መቶ ሃምሳ ሰዎች ነበር፡፡ አመጽንና ክህደትን በትክክለኛ ስማቸው ጥራ፤ ከዚያም የጥንቱ የእግዚአብሔር ሕዝብ ልምምድ ከሚያስጠሉ ባሕርያቱ ጋር በታሪክ ውስጥ እንዲያልፍ በታማኝነት መጻፉን ልብ በል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ይላል፣ «ይህ ሁሉ…እኛን የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን ሊገስጸን ተጻፈ” (1 ቆሮ. 10፡11)፡፡ የእውነት እውቀት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ታላቁን የክህደት መሪ በመውሰድ ክርስቶስ ጽድቃችን ብለው እስከሚጠሩት ድረስ ከታላቁ መሪያቸው የሚለዩበት ምክንያት ወደ እውነት ቁፋሮ ጠልቀው ካለመግባታቸው የተነሳ ነው፡፡ የከበረውን ማዕድን ተራ ከሆነው ነገር መለየት አልቻሉም፡፡ Amh2SM 393.2
ከተቻላቸው የተመረጡትን እንኳን ለማሳሳት ከመናፍቅነታቸው ጋር የሚመጡትን ሀሰተኛ ነቢያት በተመለከተ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በብዛት የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች አንብቡ፡፡ እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች እያሉ ቤተ ክርስቲያን ሀሰትን ከትክክለኛው ነገር የማትለየው ለምንድን ነው? በማንኛውም መንገድ ቢሆን ወደ ስህተት የተመሩ ሰዎች እንደዚህ በቀላሉ ወደ ስህተት በመመራታቸው በእግዚአብሔር ፊት ራሳቸውን ዝቅ ማድረግ እና ንስሃ መግባት ያስፈልጋቸዋል፡፡ የእውነተኛውን እረኛ ድምጽ እንግዳ ከሆነ ድምጽ አልለዩም፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች በሙሉ ይህኛውን የልምምዳቸውን ምዕራፍ ይከልሱ፡፡ Amh2SM 393.3
ከግማሽ ምዕተ አመት ለበለጠ ጊዜ እግዚአብሔር በምስክሮች አማካይነት ለሕዝቡ ብርሃን ሲሰጥ ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ሚስስ ኋይትን አጭበርባሪ እና አሳሳች ናት በማለት መላውን የአማኞች ቤተ ክርስቲያን ከመታለል የማዳን ኃላፊነት የተተወው ለጥቂት ወንዶችና ለሚስቶቻቸው ነው ወይ? «ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ» (ማቴ. 7፡20)፡፡ Amh2SM 394.1
እግዚአብሔር የሰጣቸውን ማስረጃዎች በሙሉ ችላ በማለት በረከትን ወደ እርግማን የሚለውጡ ሰዎች ለራሳቸው ነፍስ ደህንነት መንቀጥቀጥ አለባቸው፡፡ ንስሃ ካልገቡ በስተቀር መቅረዛቸው ከስፍራው ይወገዳል፡፡ እግዚአብሔር ሲሰደብ ነበር፡፡ የእውነት መስፈርት፣ የመጀመሪያው፣ የሁለተኛውና የሶስተኛው መላእክት መልእክቶች በአቧራ ውስጥ እንዲጎተቱ ተትተዋል፡፡ ጠባቂዎች በዚህ መልክ ሕዝቡን ወደ ስህተት እንዲመሩ ከተተዉ ለመንጋው ምን ዓይነት መኖ እየተሰጠ እንደሆነ ለይተው ማወቅ ስላልቻሉ እግዚአብሔር ተጠያቂ የሚያርጋቸው አንዳንድ ነፍሳት አሉ፡፡ Amh2SM 394.2
ከዚህ በፊት ክህደቶች ተከስተዋል፤ የዚህ ዓይነት ባሕርይ ያላቸው ነገሮች እንዲከሰቱ ጌታ የፈቀደበት ምክንያት ሕዝቡ ልክ የቤሪያ ሰዎች እንዳደረጉት ሁሉ እነዚህ ነገሮች እንዲህ መሆናቸውን ለማወቅ ለራሳቸው ቅዱሳን መጻሕፍትን ከመመርመር ይልቅ በሰዎች ቃላት በሚደገፉበት ጊዜ እንዴት በቀላሉ ወደ ስህተት እንደሚመሩ ለማሳየት ነበር፡፡ እነዚህን የመሰሉ ነገሮች እንዲከሰቱ ጌታ የፈቀደበት ምክንያት እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች እንደሚከሰቱ ማስጠንቀቂያዎች እንዲሰጡ ነው፡፡ Amh2SM 394.3