የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
መፍራት አያስፈልግም
ሥራው አይሳካም ብሎ መጠራጠርና መፍራት አያስፈልግም፡፡ ሥራውን የሚመራው እግዚአብሔር ስለሆነ ሁሉንም ነገር በሥርዓት ያስቀምጠዋል፡፡ ሥራውን በሚመሩት ዘንድ መስተካከል የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ካሉ እግዚአብሔር ጉዳዩን ተከታትሎት እያንዳንዱን ስህተት ለማስተካከል ይሰራል፡፡ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የጫነውን የከበረ መርከብ እግዚአብሔር ያለ አንዳች ችግር ከወደቡ እንደሚያደርሰው እምነት ይኑረን፡፡ Amh2SM 390.2
ከብዙ አመታት በፊት ከፖርትላንድ ሜይን ወደ ቦስተን ጉዞ ባደረግኩበት ወቅት ወጀብ ተነሳብንና ታላቅ ማዕበል ወዲህና ወዲያ ያላጋን ጀመር፡፡ ብርሃን የሚሰጡ መቅረዞች ወደቁና ዘንጎቹ እንደ ኳስ ከአንድ ወገን ወደ ሌላኛው ወገን ተንከባለሉ፡፡ መንገደኞቹ ፍርሃት ውጧቸው ብዙዎቹ ሞትን በመጠባበቅ ይጮሁ ነበር፡፡ Amh2SM 390.3
ከቆይታ በኋላ መርከብ ነጂው መርከቧን ተሳፈረ፡፡ የመርከቧ አዛዥ ከነጂው አጠገብ ቆሞ መርከቧ እየሄደች ስላለችበት መንገድ ፍርሃቱን ገለጸለት፡፡ ነጂው መሪውን መያዝ ትፈልጋለህን? ብሎ አዛዡን ጠየቀው፡፡ አዛዡ ልምድ እንደሌለው ስለራሱ ስለሚያውቅ መሪውን ለመያዝ ዝግጁ አልነበረም፡፡ Amh2SM 390.4
ያኔ መንገደኞቹ ምቾት አልተሰማቸውም፣ መሪው ከድንጋይ ጋር ያጋጨናል ብለው ፍርሃታቸውን ገለጹ፡፡ ነጂው «መሪውን መያዝ ትፈልጋላችሁን?” ብሎ ጠየቃቸው፣ ነገር ግን መሪውን መያዝ እንደማይችሉ አወቁ፡፡ Amh2SM 390.5
ሥራው አደጋ ውስጥ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ «ጌታ ሆይ፣ በመሪው አጠገብ ቁምና አደናጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ አሳልፈኸን በሰላም ወደ ወደቡ አድርሰን” ብላችሁ ጸልዩ፡፡ እግዚአብሔር በድል እንደሚያሻግረን ለማመን ምክንያት የለንምን? Amh2SM 391.1
ከፊቴ በሥራው ውስጥ ልምድ ያላቸው ብዙዎች ነበሩ፡፡ እያንዳንዳችሁን ላለፉት ሰለሳ አመታት አውቃችኋለሁ፡፡ ወንድሞቼ ሆይ፣ በሥራው ላይ ችግር እየተፈራረቀብን አላየንምን? ጌታ ለስሙ ክብር በመሥራት አላሻገረንምን? ልታምኑት አትችሉምን? ሥራውን ለእሱ አሳልፋችሁ መስጠት አትችሉምን? ውስን በሆኑ አእምሮዎቻችሁ የእግዚአብሔርን አሰራር ማስተዋል አትችሉም፡፡ እግዚአብሔር ለሥራው እንዲጠነቀቅ ተውለት፡፡ The Review and Herald, Sept. 20, 1892. Amh2SM 391.2