የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

309/349

ምዕራፍ 49—የተለየ ስም እና ሕዝብ

በስማችን አናፍርበትም

እኛ የሰባተኛ ቀን አክባሪ አድቬንቲስቶች ነን፡፡ በስማችን እናፍርበታለን ወይ? መልሳችን «በፍጹም! በፍጹም አናፍርበትም፡፡ ጌታ የሰጠን ስም ነው፡፡ የአብያተ ክርስቲያናት መፈተኛ ሊሆን ያለውን እውነት የሚያመለክት ስም ነው» የሚል ነው፡፡ Letter 110, 1902. Amh2SM 384.1

እኛ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ነን፣ በዚህ ሰም በፍጹም ማፈር የለብንም፡፡ እንደ ሕዝብ ለእውነትና ለጽድቅ የጸና አቋም መያዝ አለብን፡፡ ይህ ሲሆን እግዚአብሔርን እናከብራለን፡፡ በአደጋዎች ልንጠመድና ልንጠፋ ሳይሆን ነጻ ልንወጣ ነው፡፡ ይህ እንዲሆን የእምነታችን ጀማሪና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን መመልከት አለብን፡፡ Letter 106, 1903. Amh2SM 384.2