የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ኃጢአትን ከሕይወታችን ማስወገድ
የኩራት ኃጢአት ከእኛ ይወገድ፣ የታይታ አለባበስ ይሸነፍ፣ ወደ ሚስዮናዊ የሥራ መስኮች መፍሰስ የነበረበትን በመከልከል በእግዚአብሔር ላይ ለተፈጸመው የድፍረት ዝርፊያ ወደ እግዚአብሔር ንስሃ ይቅረብ፡፡ የተሃድሶና የእውነተኛ መለወጥ ሥራ በሰዎች ፊት ይቅረብና እንዲተገበር ግፊት ይደረግ፡፡ ሥራችንና ባሕርያችን «እኛ ክርስቶስን እንደተከተልን ተከተሉን” ማለት እንዲችል ከወቅቱ ሥራ ጋር ግንኙነት ይኑረው፡፡ በእግዚአብሔር ፊት በመዋረድ፣ በጾምና በጸሎት፣ ለኃጢአታችን በመናዘዝና ኃጢአትን በማስወገድ ነፍሳችንን ዝቅ እናድርግ፡፡ Amh2SM 379.2
«ይነጋል ደግሞም ይመሻል» (ኢሳ. 21፡ 12) የሚለው የእውነተኛ ጠባቂ ድምፅ በሁሉም አቅጣጫ አሁን መሰማት አለበት፡፡ በታላቁ የጌታ መዘጋጀት ቀን ስለሆንን መለከቱ እርግጠኛ የሆነ ድምፅ ማሰማት አለበት፡፡ በዓለማችን ውስጥ ብዙ የአስተምህሮ አዝማሚያዎች አሉ፡፡ በሺሆችና በአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ ብዙ የኃይማኖት አዝማሚያዎች አሉ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ምልክትና ማህተም የያዘ አንድ ብቻ ነው፡፡ ነፍሳችን ከዘላለም አለት ጋር መያያዝ አለበት፡፡ በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ነገር፣ ሰዎች፣ አስተምህሮዎችና ተፈጥሮ ራሱ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን እውነተኛ ትንቢት በመፈጸም በዚህ ዓለም ታሪክ ፍጻሜ ላይ የእርሱን ታላቅ የፍጻሜ ሥራ እየሰራ ነው፡፡ Amh2SM 379.3
የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለመፈጸም መዘጋጀትና መጠበቅ አለብን፡፡ መንግሥታት ከሥረ-መሠረታቸው ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡ ብቸኛ የሆነውን እውነተኛ የባሕርይ መፈተኛ፣ ብቸኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን የጽድቅ መስፈርት ለሚያውጁ ሰዎች የሚሰጥ ድጋፍ ይነሳል፡፡ ለብሔራዊ መማክርት አዋጅ የማይሰግዱ እና የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቀን ችላ በማለት በኃጢአት ሰው የተቋቋመውን ሰንበት ከፍ ከፍ ለማድረግ የወጡትን ብሔራዊ ሕጎች የማይታዘዙ ሁሉ ጨቋኝ የሆነው ጳጳሳዊ ኃይል ጭቆና ብቻ ሳይሆን የአውሬውን ምልክት የያዘው የፕሮቴስታንቱ ዓለም ጭቆናም ይደርስባቸዋል፡፡ Amh2SM 380.1
ሰይጣን ለማሳሳት ተአምራቶችን ይሰራል፤ ኃይሉን ከሁሉም በላይ አድርጎ ያስቀምጣል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የምትወድቅ ትመስላለች፣ ነገር ግን አትወድቅም፡፡ ኃጢአተኞች በጽዮን እየተበጠሩ፣ ስንዴው ከገለባ እየተለየ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ጸንታ ትቆማለች፡፡ ይህ አሰቃቂ የሆነ የመከራ ጊዜ ነው፣ ነገር ግን መሆን አለበት፡፡ ከታማኞችና እውነተኞች ጋር፣ ነቁጣ ወይም የኃጢአት እድፈት ሳይኖርባቸው፣ በአፋቸውም ነውር ሳይገኝባቸው የሚገኙ ሰዎች በበጉ ደምና በምስክርነታቸው ቃል ያሸነፉ ብቻ ናቸው፡፡ የራስ ጽድቃችን ተገፍፎ የክርስቶስን ጽድቅ መልበስ አለብን፡፡ Amh2SM 380.2