የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

303/349

ከተሰጡን እድሎች በታች መኖር

ድንቅ በሆነ ሁኔታ በተገለጸልን የእግዚአብሔር እውነት እና ከዓላማዎቹ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ ነፍሳችንን ስለማናሳድግና ባሕርያችንን ስለማናሻሽል ያለነው እግዚአብሔር እንደ ሕዝብ እንድንሆን ከሚፈልግብን ሁኔታ ርቀን ነው፡፡ «ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኃጢአት ግን ሕዝብን ታስነውራለች” (ምሳሌ 14፡ 34)፡፡ ኃጢአት አቃዋሽ ወይም አዝረክራኪ ነው፡፡ በግለሰብ ልብ ውስጥ፣ በቤተሰብ ውስጥ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወይም በማንኛውም ኃጢአት ከፍተኛ ቦታ በተሰጠው ሥፍራ ሁሉ የሰው እና የእግዚአብሔር ጠላት አእምሮን የመቆጣጠር ኃይል ስላለው መዝረክረክ፣ መለያየት፣ ጠላትነት፣ ቅንዓትና ምቀኝነት አለ፡፡ ነገር ግን ወንድም ሆነ ሴት ኃጢአትን እንዲጠላ/ትጠላ እና ለዓለም የኢየሱስ ክርስቶስ ወኪል እንዲሆን/እንድትሆን እውነት መወደድ እና በሕይወት ውስጥ ቦታ ማግኘት አለበት፡፡ Amh2SM 377.2

እውነትን እንደሚያምኑ የሚናገሩ ሕዝቦች የሚኮነኑት ብርሃን ስላልነበራቸው ሳይሆን ከፍተኛ ብርሃን ተሰጥቷቸው ሳለ የእግዚአብሔር ጽድቅ ወደሚጠይቀው ከፍተኛ የግብረገብ መስፈርት መፈተኛ ልባቸውን ስላላመጡ ነው፡፡ እውነትን እናምናለን የሚል ሕዝብ በዚያ እውነት በመኖር ከፍ ከፍ ማለት አለበት፡፡ ትክክለኛ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት ሕይወትን መለወጥ፣ ባሕርይን ማንጻትና የከበረ ማድረግ፣ የበለጠ መለኮት የሚፈልገው ዓይነት እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡ ያኔ ቤት ለእግዚአብሔር ምሥጋናና ውዳሴ ሲያቀርብ ይሰማል፡፡ በቤት ውስጥ መላእክት ያገለግላሉ፣ አምላኪዎቹንም ወደ ጸሎት ቤት ያጅቡአቸዋል፡፡ Amh2SM 377.3

እውነትን እናምናለን የሚሉና የእግዚአብሔርን ሕግ ትክክለኛነት የሚቀበሉ ቤተ ክርስቲያናት ሕጉን ይጠብቁ፣ ከአመጻም ይራቁ፡፡ እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ክፉን እንዲለማመድና ኃጢአትን እንዲፈጽም የሚያደርገውን ፈተናዎች ይቋቋም፡፡ ያለነው ዘላለማዊ ውጤቶችን ባዘለ አስፈሪ ሰዓት፣ በምሳሌያዊው የስርየት ቀን ውስጥ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት በንስሃ፣ ራስን በማዋረድ፣ በጥልቀት ልብን በመመርመር የማንጻት ሥራን መጀመር አለባት፡፡ Amh2SM 378.1

እውነትን የሚያስተምሩ ሰዎች ያን እውነት ልክ በክርስቶስ እንዳለ ያቅርቡ፡፡ በእግዚአብሔር እውነት ራስን የማስገዛት፣ የመቀደስና የማንጻት ተጽዕኖ ሥር ሲሆኑ እንደ ንጹህ ዕቃዎች ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት እርሾ ይለወጡ፡፡ ያኔ ከእነርሱ ወደ ዓለም እንዴት ያለ ተጽዕኖ ይሄድ ይሁን! እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል ንጹህ፣ ጽኑ፣ የማይነቃነቅና ሁልጊዜ በኢየሱስ ፍቅር የሚኖር መሆን አለበት፡፡ ያኔ ለዓለም ብርሃን ይሆናሉ፡፡ ጠባቂዎችና የመንጋው እረኞች የሆኑ ሰዎች እውነትን ያውጁ፤ ለሕዝብ፣ ለወገን፣ ለቋንቋ ሁሉ የማስጠንቀቂያ ድምጽ ያሰሙ፡፡ ለሚያምኑት እውነት ሕያው ወኪሎች ይሁኑ፤ በእግዚአብሔር ፊት በንጽህና እና በቅድስና በመመላለስ ጥብቅ እና ቅዱስ በሆነ መስማማት የእግዚአብሔርን ሕግ ያክብሩ፡፡ ያኔ ብርሃንን በየቦታው የሚያንጸባርቀውን የእውነት አዋጅ ኃይል ይከተለዋል፡፡ Amh2SM 378.2