የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ከተሞችን ለመልቀቅ እያሰላሰሉ ላሉት የተሰጠ ምክርና ማስጠንቀቂያ
ወንድሜ ሆይ፣ ከባትል ክሪክ ለመውጣት በጥልቀት የተነሳሱ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ደብዳቤህ ይነግረኛል፡፡ ይህ ሥራ እንዲሰራ ከፍተኛ አስፈላጊነት ያለ ሲሆን መሆን ያለበትም አሁን ነው ፡፡ በመጨረሻ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የተሰማቸው ሰዎች በጥድፊያ፣ በግርግር፣ ወይም በችኮላ ወይም ኋላ በመውጣታቸው ምክንያት ጥልቅ ቁጭት በሚፈጥርባቸው ሁኔታ አያድርጉት፡፡… Amh2SM 361.1
ከባትል ክሪክ ለመውጣት የተሰጠውን ምክር በማዳመጥ የችኮላ እንቅስቃሴዎች እንዳይኖሩ ልብ በሉ፡፡ ለሚጠይቁት ሁሉ ሳይነፍግ በልግስና ለመስጠት ቃል ከገበው እግዚአብሔር ጥበብን ሳትፈልጉ ምንም ነገር አታድርጉ፡፡ ማንም ሰው ቢሆን ማድረግ የሚችለው ነገር ቢኖር፣ ጉዳዩን በተመለከተ በመለኮታዊ ምሪት ለመንቀሳቀስ ያመኑትን፣ ለመማርና እግዚአብሔርን ለመታዘዝ በሙሉ ልባቸው ክፍት የሆኑትን መምከርና መተው ነው፡፡ Amh2SM 361.2
ከመምህራኖቻችን መካከል እንኳን አንዳንዶቹ ትክክለኛ ውሳኔ ማድረግን በተመለከተ የበለጠ ሚዛናዊ መሆን እንደሚገባቸው ሳስብ ተረብሻለሁ፡፡ የምህረት መልእክትን ለዓለማችን የሚያደርሱ መልእክተኞች፣ የሕዝብ አመኔታ ያላቸው፣ ምክር የሚሹ ናቸው፡፡ በተግባር የተደገፈ ሕይወት ምን እንደሚመስል ትክክለኛ የሆነ ልምምድ የሌላቸው ሰዎች፣ የሚሰጡት ምክር ሌሎች ምን እንዲያደርጉ እንደሚመራቸው ሳያውቁ ምክር በመስጠት አደጋ ውስጥ ያሉ ሰዎች ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡ Amh2SM 361.3
አንዳንድ ሰዎች በጉዳዩ ላይ የመረዳት ችሎታ ስላላቸው የመምከር ችሎታም ይኖራቸዋል፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ሥራ ትክክለኛ፣ ክቡርና ጽኑ ቃላት በሚያስፈልጉበት ወቅት፣ ግራ የተጋቡና በጨለማ ውስጥ ያሉ አእምሮዎች መከተል ያለባቸውን መንገድ እንደ ፈጣን የፀሐይ ብርሃን ብልጭታ እንዲያዩ የሚመሩ ቃላትን መናገር ይችላሉ፡፡ መንገዱ ግራ ያጋባቸውና ለሳምንታትና ለወራት በማጥናት አእምሮአቸውን ያስጨነቀ ነው፡፡ መግለጥና በፊታቸው መንገድን ማጥራት አለ፣ ጌታ ከእርሱ የሆነው የፀሐይ ብርሃን እንዲገባ ስላደረገ ጸሎታቸው ተመልሶ፣ መንገዳቸውም ጠርቶ ያያሉ፡፡ ነገር ግን ብቻ ከባትል ክሪክ ውጡ የሚል የሆነ የችኮላ ምክር ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይህን በማድረግ ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች መንፈሳዊ ዕድገት ምን መሻሻል እንደሚያመጣ በግልጽ የተሰጠ ምንም ነገር ሳይኖር እንደዚህ ያለ ምክር ይሰጣሉ፡፡ Amh2SM 361.4