የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

286/349

ከከተማ ራቅ ብለው ካሉ ጣቢያዎች ሆኖ ለከተሞች መሥራት

በተቻለ መጠን ተቋሞቻችን ከከተሞች መራቅ አለባቸው፡፡ ለእነዚህ ተቋማት ሰራተኞች ስለሚያስፈልጉ ተቋሞቹ ከተማ ውስጥ ከሆኑ የሕዝባችን ቤተሰቦች በተቋሞቹ አጠገብ መኖር አለባቸው፡፡ ነገር ግን የማያቋርጥ ሕውከትና ውዝግብ ባሉባቸው ከተሞች ውስጥ ሕዝቡ እንዲኖር የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ መላው ሥርዓት በጥድፊያ፣ በችኮላ እና በጩኸት የተበላሸ ስለሆነ ልጆቻቸው ከዚህ መዳን አለባቸው፡፡ ሕዝባችን በመሬት ላይ መስፈር ወደሚችሉበት፣ የራሳቸውን ፍራፍሬና አትክልት ማሳደግ ወደሚችሉበትና ልጆቻቸው በተፈጥሮ ውስጥ ካሉት የእግዚአብሔር ሥራዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መፍጠር ወደሚችሉባቸው ወደ ገጠር አከባቢዎች እንዲሄዱ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ ቤተሰቦቻችሁን ከከተሞች ራቅ ወዳሉ ቦታዎች ውሰዱ የሚለው መልእክቴ ነው፡፡ Amh2SM 357.4

ሰዎች ቢሰሙም ባይሰሙም እውነት መነገር አለበት፡፡ ከተሞች በፈተናዎች ተሞልተዋል፡፡ ሥራችንን ማቀድ ያለብን በተቻለ መጠን ወጣቶቻችንን ከዚህ ብክለት ማራቅ በምንችልበት ሁኔታ ነው፡፡ Amh2SM 358.1

ለከተሞች መሥራት ያለብን ራቅ ካሉ ከተሞች በመነሳት ነው፡፡ የእግዚአብሔር መልእክተኛ እንዲህ ብሏል፣ «ከተሞች ማስጠንቀቂያ አይሰጣቸውምን? ይሰጣቸዋል፤ ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው በውስጣቸው በሚኖር የእግዚአብሔር ሕዝብ ሳይሆን በምድር ላይ እየመጣ ያለውን ነገር ለማስጠንቀቅ በሚጎበኙአቸው ሰዎች ነው፡፡» Amh2SM 358.2