የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
የተሳሳተ መንገድን መከተል ያስከተላቸውን ውጤቶች ለማጥፋት ተአምራትን አትጠብቁ
እነዚህን አበባዎች እመለከትና እነርሱን ባየኋቸው ሰዓት ሁሉ ኤድንን አስባለሁ፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር መግለጫ ናቸው፡፡ በመሆኑም በዚህች ዓለም ላይ የኤድንን ቅምሻ ይሰጠናል፡፡ እሱ በፈጠራቸው ውብ ነገሮች እንድንደሰትና በእነርሱ ውስጥ እርሱ የሚያደርግልንን ነገሮች መግለጫ እንድናይ ይፈልጋል፡፡ Amh2SM 356.2
ለመሥራትም ሆነ ለመንቀሳቀስ በቂ ቦታ ልናገኝ በምንችልበት ቦታ እንድንኖር ይፈልጋል፡፡ ሕዝቡ በከተማዎች ውስጥ መጨናነቅ የለባቸውም፡፡ ለዘላለማዊ ሕይወት በተሻለ ሁኔታ መዘጋጀት እንዲችሉ ቤተሰቦቻቸውን ከከተማ እንዲያስወጡ ይፈልጋል፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተማዎችን መልቀቅ ሊኖርባቸው ነው፡፡ Amh2SM 356.3
እነዚህ ከተማዎች እያንዳንዱ ዓይነት ኃጢአት፣ የሥራ ማቆም አድማ፣ ነፍስ ግድያና ራስን ማጥፋት የሞላባቸው ናቸው፡፡ ሰይጣን ሰዎችን በጥፋት ሥራቸው እየተቆጣጠራቸው ያለው በከተማዎች ውስጥ ነው፡፡ በእርሱ ተጽእኖ መግደል ስለሚፈልጉ ብቻ የሚገድሉ ሲሆን ይህ ድርጊት እየጨመረ ይሄዳል፡፡… Amh2SM 356.4
ራሳችንን በእነዚህ የሚያስጠሉ ተጽእኖዎች ሥር ካስቀመጥን፣ መጥፎ ድርጊቶቻችን ያስከተሏቸውን ውጤቶች ለማጥፋት እግዚአብሔር ተአምር እንዲሰራ መጠበቅ እንችላለንን? በፍጹም መጠበቅ አንችልም፡፡ በተቻለ ፍጥነት ከትልልቅ ከተማዎች ውጡና የአትክልት ቦታ ሊኖራችሁ በሚችልበት፣ ልጆቻችሁ አበቦች ሲያድጉ ማየት በሚችሉበት እና ከእነርሱ የትህትናንና የንጽህናን ትምህርት መማር በሚችሉበት ቦታ ትንሽ መሬት ግዙ፡፡ General Conference Bulletin, March 30, 1903. Amh2SM 356.5