የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

279/349

በሰመመን ውስጥ ስለ መግባት የተጻፉ መጻሕፍትን በተመለከተ የተሰጠ ምክር

(ለዓመታት በማተሚያ ቤታችን ውስጥ የወንጌል መልእክትን ለማሳተም የተገዙ መሳሪያዎችን ትርፋማ በሆነ ሁኔታ ለመጠቀም በሚደረግ ጥረት ውስጥ የተወሰነ መጠን ያለው የንግድ ሥራ ተወስዷል፡፡ ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ የጎጂነት ባሕርይ ያላቸው ነገሮች ለሕትመት የተወሰዱበት ጊዜ መጥቶ ነበር፡፡ ለዚህ አሳዛኝ ልምምድ ዋቢ የሚሆኑ ነገሮች በቴስቲሞኒስ ቅጽ 7፣ ገጽ 164-168 እና ሰመመንን በተመለከተ በታተመው ስለ ሥነ-ጽሁፍ በሚናገረው ቀጥሎ በነበረው ነገር ውስጥ ተሰጥቷል፡፡ አዘጋጆች፡፡) Amh2SM 350.4

ሰዎችን ወደ ሰመመን ስለማስገባት የሚያስተምሩ መጻሕፍትን በማሳተም ሥራ መሪዎቹ ከሰይጣን ወኪሎች ጋር ስምምነት ይፈጥራሉን? ይህ ለምጽ ወደ ቢሮ መግባት አለበትን?...ሰይጣንና ወኪሎቹ ተግተው ሲሰሩ ነበር፣ አሁንም እየሰሩ ናቸው፡፡ ማተሚያ ቤቶች የጠላትን ማታለያዎች ከተቀበሉ እግዚአብሔር በረከቱን ይሰጣቸዋልን? በሰዎች ፊት ለጌታ ቅዱስ ሆነው የተጠበቁ ተቋማት ሰራተኞች የተከለከለውን ክፉንና ደጉን የምታስታውቀውን ዛፍ ፍሬ የሚበሉባቸው ትምህርት ቤቶች ይሆናሉን? ሰይጣን በኤደን እንዳደረገው ገሃነማዊ ሳይንሱን በእውነት ምሽግ ውስጥ ለማስቀመጥ ተደብቆ እንዲገባ እናደፋፍራለንን? በሥራው ዕንብርት ውስጥ ያሉ ሰዎች በእውነትና በሀሰት መካከል መለየት የማይችሉ ናቸውን? የመጥፎ ነገር ተጽእኖ ማሳደር የሚያስከትለውን አሰቃቂ ውጤት ማየት የማይችሉ ሰዎች ናቸውን? Amh2SM 350.5

የሰይጣን ውሸቶች በሕዝብ ዘንድ እውቅና እንዲያገኙ ስህተትን የያዙ መጻሕፍትን ለዓለም ለማሰራጨት የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ማተሚያ ቤትን ዓለም አሳትም ብሎ እንዲናገር መፍቀድ የሚያስከትለው አሰቃቂ ኪሳራ ቤተ ክርስቲያኗ ይህን ሥራ በመሥራት ከምታገኘው በሚሊዮኖች ከሚቆጠሩ ዶላሮች ጋር ሲነጻጸር ትርፉ ምን ዋጋ አለው? Amh2SM 351.1

ማተሚያ ቤቶቻችሁ የሰይጣንን ውሸቶች እንዳተሙ ነቅታችሁ ተገንዘቡ፡፡ እውነትን የሚያውቁ ሰዎች የተጽእኖአቸውን ሙሉ ክብደት በእውነትና በጽድቅ በኩል በማስቀመጥ እንደ ጠቢባን ሰዎች ይስሩ፡፡ Letter 140, 1901 (Addressed to the managers of our publishing house, oct. 16, 1901). Amh2SM 351.2