የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ወደ ጤንነት መመለስ የተሻለ የማይሆንበት ጊዜ
በሕመም የሚሰቃይ ሰብአዊነትን ጉዳይ እግዚአብሔር በሕዝቡ ልብ ውስጥ በማስቀመጡና በውስጣቸው የሚናፍቅ ነፍስ በማስቀመጡ እግዚአብሔር የገባውን ቃል እንዲፈጽም ለመጠየቅ መብት እንዳላቸው በማሰብ ፈውስ እንዲመጣ እጅግ በታማኝነት ጸሎት ቢያደርጉም ሕመምተኛው የሞተበትን አጋጣሚ እናውቃለን፡፡ መጨረሻውን ከመጀመሪያው የሚመለከት ጌታ በኃይሉ ሕመምተኛውን ለመፈወስ ቢሰራ ኖሮ መለኮታዊው ፈቃድ የተሳሳተ ግንዛቤ እንደሚያገኝ አስተውሎ ነበር፡፡ Amh2SM 347.4
አንዳንድ ጊዜ፣ ለጓደኞችም ሆነ ለቤተ ክርስቲያን፣ ጤንነት ወደ ቀድሞ ሁኔታ መመለስ የተሻለ የማይሆንበት፣ ነገር ግን አንዳንዶች ስሜታዊነት የእምነት መሰረት ነው ብለው እንዲደመድሙ በመምራት ሥርዓት የሌለውን ፍላጎትና አክራሪነት ይፈጥራል፡፡ ከአደጋ ነጻ የሆነ ብቸኛው መንገድ የተጻፈውን ቃል መከተል ነው፡፡ በሕመም እየተሰቃየ ላለ ሰው ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ ካደረጋችሁ በኋላ ጉዳዩን በጌታ እጆች አስቀምጡ፡፡ ሞት ለእርሱ ክብር ሊሆን ይችላል፡፡ ለወራትና ለዓመታት በሕመም ላይ የነበሩትን አንዳንድ ሰዎች እንዲሞቱ ይፈቅዳል፡፡ እየተሰቃዩ ላሉት ልጆቹ እረፍት መስጠት ተገቢ እንደሆነ ያያል፡፡ Manuscript 67, 1899. Amh2SM 348.1