የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ትክክለኛ መንገድ ሊመስል ይችላል
የእግዚአብሔር ተአምራቶች ሁልጊዜ በውጭ የተአምራት መልክ አይኖራቸውም፡፡ ብዚ ጊዜ ክስተቶች የሚከተሉትን የተፈጥሮ መንገድ የተከተሉ መስለው ይመጣሉ፡፡ ለሕመምተኞች ስንጸልይ ለእነርሱ ደግሞ እንሰራለን፡፡ ልናገኛቸው የምንችላቸውን መድሃኒቶች በመጠቀም ለጸሎቶቻችን ምላሽ እንሰጣለን፡፡ ውኃ በትክክል ጥቅም ላይ ከዋለ እጅግ ኃይለኛ የሆነ ፈዋሽ ነው፡፡ በማስተዋል ጥቅም ላይ በዋለበት ቦታ ጥሩ የሆኑ ውጤቶች ታይተዋል፡፡ እግዚአብሔር እውቀት ስለሰጠን እሱ የሰጠንን ጤና ሰጭ በረከቶች በደንብ እንድንጠቀምባቸው ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ለተራቡት እንጀራ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፤ ከዚያ በኋላ ረሀባቸውን ለማስታገስ እንደ እግዚአብሔር ረዳት እጅ ሆነን እንሰራለን፡፡ በአደጋ ውስጥ ያሉትን ነጻ ለማውጣት እግዚአብሔር የሰጠንን እያንዳንዱን በረከት መጠቀም አለብን፡፡ Amh2SM 346.3
የተፈጥሮ መንገዶች ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በተስማማ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሲውሉ ከተፈጥሮ በላይ የሆኑ ውጤቶችን ያመጣሉ፡፡ እኛ ለተአምር ስንጸልይ ጌታ አእምሮአችንን ቀላል ወደሆነ መድሃኒት ይመራል፡፡ በዓለም ውስጥ በትልቅ ኃይል አድብቶ ከሚጠብቅ፣ በጨለማ ከሚሄድ ቸነፈር እንድንጠበቅ እንጠይቃለን፤ ከዚያ በኋላ የጤናና የሕይወት ሕጎችን በመጠበቅ ከእግዚአብሔር ጋር እንተባበራለን፡፡ እኛ ልናደርግ የምንችለውን ሁሉ ካደረግን በኋላ ጤንነትና ብርታት እንዲሰጠን በእምነት መጠየቃችንን መቀጠል አለብን፡፡ የአካል ጤናን የሚጠብቅ ምግብ መመገብ አለብን፡፡ እግዚአብሔር እኛ ለራሳችን ማድረግ የምንችለውን ነገር አደርግላችኋለሁ በማለት አያደፋፍረንም፡፡ የተፈጥሮ ሕጎችን መታዘዝ አለብን፡፡ ድርሻችንን ለማድረግ መስነፍ የለብንም፡፡ ጌታ እንዲህ ይላል፡- «በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነውና” (ፊል. 2፡ 12፣ 13)፡፡ Amh2SM 346.4
የእግዚአብሔርን ሕግጋት ችላ ሳንል የተፈጥሮ ሕጎችን ችላ ማለት አንችልም፡፡ ተገቢ እና ተስማሚ በሆነ ሁኔታ ጥቅም ላይ ቢውሉ ኖሮ ተአምራዊ ውጤት የሚያመጡትን እግዚአብሔር የሰጠንን ቀላል መድኃኒቶች ለመጠቀም ችላ ብለን እግዚአብሔር ተአምር እንዲሰራ መጠበቅ አንችልም፡፡ Amh2SM 346.5
ስለዚህ ጸልዩ፣ እመኑ፣ ሥሩ፡፡ Letter 66, 1901. Amh2SM 347.1