የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

267/349

ምዕራፍ 40—ጌሾ፣ትምባሆና አሳማ

ለሚነሱ ብዙ ጥያቄዎች መልስ እንዲሆን እኔ ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ጌሾን፣ ትንባሆንና አሳማን ከማሳደግ ይልቅ ከእምነታቸው ጋር የበለጠ አብሮ የሚሄድ ለኑሮአቸው ማድረግ ያለባቸው ሥራ እንዳለ እናምናለን፡፡ Amh2SM 338.1

በእርሻቸው ውስጥ ጌሾንና ትንባሆን እንዳያሳድጉና የአሳማዎችን ቁጥር እንዲቀንሱ አስተያየት እንሰጣለን፡፡ ብዙ አማኞች እንደሚያደርጉት ሁሉ ከዚህ በኋላ አለመጠበቅ ግዴታቸው እንደሆነ አድርገው ሊያዩ ይችላሉ፡፡ ይህንን አመለካከት እንዲይዝ ማንንም አንገፋፋም፡፡ «የጌሾና የትንባሆ ማሳችሁን እረሱና አሳማዎቻችሁን ለውሾች መስዋዕት አድርጉ» የሚለውን አባባል በተመለከተ የምንቀበለው ሀላፊነት እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ Amh2SM 338.2

በሕዝባችን መካከል ጌሾ፣ ትንባሆና አሳማ ከሚያሳድጉ ሕዝብ ጋር ግንኙነት ላላቸው ሰዎች እነዚህን ነገሮች፣ በምንም መልኩ ቢሆን፣ የክርስቲያን ሕብረት መፈተኛ እንዳያደርጉ እየነገርን፣ እነዚህ መጥፎ ነገሮች በእጃቸው ያሉ ሰዎችን ደግሞ «ከእምነታቸው ጋር በሚጣጣም መልኩ በተሃድሶ ጉዳይ ላይ የሕትመት ሥራቸውም ሆነ የቃል ትምህርታቸው ብዙ የተናገረ ሰዎች እንደገለጹት ብዙ ኪሳራ ሳይደርስባችሁ ከእጃችሁ ማውጣት ከቻላችሁ በተቻለ ፍጥነት እነዚህን ነገሮች ከእጃችሁ ማስወጣት አለባችሁ” እንላለን፡፡ The Review and Herald, March 24, 1868. Amh2SM 338.3