የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ምዕራፍ 37—ቤቶች የሌሉአቸው አዛውንቶች
መኖሪያ ቤት ስለሌላቸው አዛውንት ያለማቋረጥ ልመና እየቀረበ ባለበት ጉዳይ ላይ ለመነጋገር በዘጠኝ ሰዓት ላይ ከጥቂት ወንድሞች ጋር በትልቁ ድንኳን ውስጥ እንሰበሰባለን፡፡ ምንድን ነው የሚደረግላቸው? Amh2SM 331.1
ጌታ ሰጥቶኝ የነበረው ብርሃን ተደግሞልኝ ነበር፡- እያንዳንዱ ቤተሰብ ለመኖር በቂ የሆነ ነገር በመስጠት ለዘመዶቹ እንክብካቤ ያድርግ፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ሸክሙን መሸከም አለባት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልግስናን ስትለማመድ እግዚአብሔር ይባርካታል፡፡ ድሆች የእግዚአብሔር ስለሆኑ ሃዘንተኞችና ምስኪኖች እንዲሆኑ መተው የለባቸውም፡፡ Amh2SM 331.2
ቤተ ክርስቲያን ይህን ማድረግ ካልቻለች ኮንፍራንስ ሀላፊነትን መውሰድና ችግረኞች ለሆኑ የጌታ ልጆች አስፈላጊውን ማድረግ አለባት፡፡ ወላጅ ለሌላቸውም ለኑሮ አስፈላጊ የሆነ ነገር ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ወላጅ አልባ ልጆችን ዘመዶቻቸው ሊንከባከቡአቸው ካልቻሉ ቤተ ክርስቲያን ወይም ኮንፍራንስ ሊንከባከባቸውና ምቹ በሆኑ ቤቶች ውስጥ ሊያስቀምጧቸው ይገባል፡፡ Manuscript 151, 1898. Amh2SM 331.3