የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ምዕራፍ 36—ለችግር ቀን መዘጋጀት
ሥርዓት ያለው ቁጠባ ተመከረ
በሕመም ምክንያት ካልሆነ በስተቀር መጠቀም የሌለብህን አምስት ወይም አስር ዶላር በማይነካ ቦታ በየሳምንቱ አስቀምጥ፡፡ ስትቆጥብ የሆነ ነገርን ለትርፍ ማስቀመጥ ትችላለህ፡፡ ጥበብ ባለው አያያዝ ዕዳዎችህን ከከፈልክ በኋላ የሆነ ነገር መቆጠብ ትችላለህ፡፡ Letter 29, 1884 Amh2SM 329.1
በሳምንት ሃያ ዶላር የሚያገኝና ምንም ሳያስቀር ሁሉንም የሚጠቀም ቤተሰብ አውቃለሁ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የቤተሰብ አባላቱ ቁጥር ከዚህ ጋር እኩል ሆኖ ሳለ በሳምንት ውስጥ አሥራ ሁለት ዶላር የሚያገኝና አስፈላጊ ቢመስሉም ሊተዉ የሚችሉ ነገሮችን ከመግዛት በመቆጠብ በሳምንት ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ዶላር የሚቆጥብ ቤተሰብ አውቃለሁ፡፡ Amh2SM 329.2