የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
የመንፈሳዊነት አደጋዎች
በእነዚህ ጨዋታዎች ውስጥ ዓይን በእግዚአብሔር ክብር ላይ ትኩረት አድርጓልን? እንደዚህ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን መንገድና አላማዎች ያለማየት ሁኔታ አለ፡፡ በዚህ የመጠበቂያ ጊዜ ውስጥ አስተዋይ ፍጡራንን ሥራ ላይ ማዋል የተገለጸውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመቅደም በእሱ ፋንታ ሰይጣን በራሱ መንፈስ ለመሙላት በአጠገቡ ቆሞ የሰብዓዊ ወኪሎችን ግምቶችና ፈጠራዎች እየተካ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በአጠገባችሁ ጠብቁ፡፡ በእሱ በመመራት ጠቢባን፣ የማታወላውሉ፣ የማትነቃነቁ፣ ሁልጊዜ የጌታ ሥራ የበዛላችሁ ትሆናከላችሁ፡፡ በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ለጸሎት የነቃን መሆን አለብን፡፡ የሰማይ ጌታ የሆነው እግዚአብሔር የብዙዎችን አእምሮ እየማረኩ ባሉ ጨዋታዎች ውስጥ የበላይነትን ለማግኘት የጎለበተውን የሚቃጠል ስሜት ይቃወማል፡፡ Amh2SM 324.1
የህክምና ትምህርትህን በአን አርቦር እየተማርክ በነበርክበት ጊዜ ከነበረው የበለጠ አስጊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሆንክበት ሌላ ጊዜ የለም፡፡ ሰይጣን ነፍስን ለመማረክ የማይረቡ ፈተናዎችን ይዞ ለመግባት አጋጣሚዎችን መጠቀም የሚችልበትን እያንዳንዱን መንገድ እየተመለከተ ነው፡፡ ራሳቸውን ክርስቲያኖች ነን ብለው በሚጠሩ እጅግ አስተዋይ ሰዎች ውስጥ አረመኔያዊ አስተሳሰብ ያጋጥማል፡፡ አስተምህሮዎቹን ብትታዘዝ ከእግዚአብሔር ዙፋን ጋር ስለሚያቆራኙህ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በተገለጸው ጥበብ ላይ ተጣበቅ፡፡ Amh2SM 324.2
ከማንኛውም ጊዜ ይልቅ አሁን ያለንበት ጊዜ የሚፈራበት ምክንያት ክርስቲያኖች፣ እንደግለሰቦች፣ ምሳሌያቸው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ከመመልከት ይልቅ ራሳቸው በለኮሱት የብርሃን ፍንጣቂዎች መራመድ ምንም አደጋ እንደሌለበት በማሰብ እና ይህ የእግዚአብሔር መንገድ ነው በማለት ነፍሳቸውን በማታለል ነፍሳቸውን ከእግዚአብሔር ሊለዩ ስለሚችሉ ነው፡፡ Amh2SM 324.3