የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

251/349

ምዕራፍ 34—ጠቃሚ የሆነ ሥራ ከጨዋታዎች ይሻላል

ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስተማር ስህተት ከሆኑ ዘመናዊ ልምምዶች ነጻ አድርገው እንዲያሳድጓቸው አስተምሯቸው፡፡ ሴት ልጆች ጠቃሚ የሆነ የቤት ውስጥ ሥራን ብቻ ሳይሆን የውጭ ሥራንም መስራት እንዲችሉ በእናቶቻቸው ሥር ሆነው መማር አለባቸው፡፡ እናቶች ወንዶች ልጆችንም ቢሆን እስከተወሰነ እድሜ ድረስ ጠቃሚ የሆኑ የቤት ውስጥንም ሆነ የውጭ ሥራን እንዲሰሩ ማሰልጠን ይችላሉ፡፡ Amh2SM 321.1

ደስታን ለማግኘት ተብሎ የሚደረጉ መዝናኛዎችን ሙሉ በሙሉ አለአስፈላጊ እንዲሆኑ የሚያደርጉ መሰራት ያለባቸው በርካታ አስፈላጊና ጠቃሚ ነገሮች በዓለም ውስጥ አሉ፡፡ እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ እርሱ የሰጣቸውን መክሊቶች ተግባራዊ በሆነ ጥቅም ላይ በማዋል የአእምሮ ኃይሎችን ለማጎልበትና የአካል ክፍሎችን ለማጠንከር ጠንከር ያሉ ጥሩ ሀሳቦችን በማሰብ ወጣቶችን ሊያሰለጥኑ የሚችሉ እቅዶችን በመቀየስ ለዓላማ ስንጠቀማቸው አእምሮ፣ አጥንትና ጡንቻ ጥንካሬና ብርታት ያገኛሉ፡፡ Amh2SM 321.2

የጤና ተቋማችንና ኮሌጃችን በመካከላችን እንዲቋቋሙ አስገዳጅ የሆነው ምክንያት ይህ መሆኑ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን በሎጥና በኖህ ዘመን እንደነበረው ሁሉ በእኛ ዘመንም እንዲሁ ነው፡፡ ሰዎች ብዙ አዲስ ግኝቶችን በመፈለግ ከእግዚአብሔር ዓላማና ፈቃድ በስፋት ርቀዋል፡፡ Amh2SM 321.3