የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
ጉዳት የማያስከትሉ ቀላል ፈውሶች
ለራሳችን ማድረግ የምንችለውን ነገር በተመለከተ ጥንቃቄ የተሞላበትን ማሰብ የሚጠይቅ ነጥብ ነው፡፡ ከራሴ ጋር በደንብ መተዋወቅ አለብኝ፤ ይህን ሕንፃ፣ እግዚአብሔር የሰጠኝን አካል፣ ጤንነቱን በጣም ጥሩ በሆነ ሁኔታ ለመጠበቅ እንዴት ባለ ሁኔታ መጠንቀቅ እንዳለብኝ ሁልጊዜ መማር አለብኝ፡፡ ለአካሌ እጅግ በጣም ጥሩ የሆኑ ነገሮችን መመገብ አለብኝ፡፡ በልብስ ምርጫዬም ጤናማ የሆነ የደም ዝውውርን የሚፈቅዱ ልብሶችን በጥንቃቄ መምረጥ አለብኝ፡፡ ለሰውነቴ እንቅስቃሴንና አየርን መንፈግ የለብኝም፡፡ ማግኘት የምችለውን ያህል የጸሐይ ብርሃን ማግኘት አለብኝ፡፡ Amh2SM 296.3
ለአካሌ ታማኝ ጠባቂ ለመሆን ጥበብ ሊኖረኝ ይገባል፡፡ እያላበኝ ሳለ ቀዝቃዛ ወደ ሆነ ክፍል መግባት ጥበብ ማጣት ነው፣ ንፋስ ባለበት ቦታ ተቀምጬ ራሴን ለቅዝቃዜ ማጋለጥ ለራሴ ጥበብ የጎደለኝ መጋቢ መሆኔን ያሳያል፡፡ እግሮቼንና እጆቼን ለቅዝቃዜ አጋልጬ በመቀመጥ ከእነዚህ ራቅ ካሉ የአካል ክፍሎች ደምን ወደ አእምሮ ወይም የውስጥ አካል ክፍሎች ብልክ ጥበብ የለኝም ማለት ነው፡፡ የአየር ንብረቱ እርጥበት ካለው ሁልጊዜ እግሮቼን ከቅዝቃዜ መከላከል አለብኝ፡፡ Amh2SM 296.4
እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥራት ያለውን ደም ሊፈጥር የሚችል እጅግ በጣም ጤናማ የሆነ ምግብን በመደበኛነት መመገብ አለብኝ፣ የሚቻል ከሆነ ደግሞ ከመጠን በላይ መሥራት የለብኝም፡፡ Amh2SM 297.1
እግዚአብሔር በአካሌ ውስጥ ያስቀመጣቸውን ሕጎች በምጥስበት ጊዜ መናዘዝና መታደስ፣ ራሴንም እግዚአብሔር በሰጣቸው ሐኪሞች፣ ማለትም ንፁህ አየር፣ ንፁህ ውኃ፣ እና ፋዋሽ በሆነው ውድ የፀሐይ ብርሃን ሥር ማስቀመጥ አለብኝ፡፡ Amh2SM 297.2
ውኃ ሥቃይን ለማስታገስ በብዙ መንገድ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ ከምግብ በፊት የሚወሰድ ንፁህ ሙቅ ውኃ (ግማሽ ሊትር፣ ከዚያ በላይ ወይም በታች ሊሆን ይችላል) መልካም ውጤት ከማስገኘቱ በስተቀር ምንም ጉዳት የለውም፡፡ Amh2SM 297.3
ከጦስኝ (catnip) ቅጠል የተሰራ አንድ ብርጭቆ ሻይ ነርቮችን ጸጥ ያሰኛል፡፡ የጌሾ ሻይ እንቅልፍ ያስይዛል፡፡ የደቀቀ ጌሾ በጨርቅ ተጠቅልሎ በውኃ ተነክሮ በሆድ ላይ ሲደረግ ሕመም ያስታግሳል፡፡ Amh2SM 297.4
ዓይኖች ደካማ ከሆኑ፣ በዓይኖች ውስጥ እብጠት ወይም ሕመም ካለ፣ በትኩስ ውኃ የራሰ እና ጨው የተደረገበት፣ ሙቀት የሚሰጥ ለስላሳ ጨርቅ ሕመሙን በፍጥነት ያስታግሳል፡፡ Amh2SM 297.5
አእምሮ ሲጨናነቅ ትንሽ ሰናፍጭ ባለበት ውኃ ውስጥ እግሮችና እጆች ሲነከሩ እፎይታ ይገኛል፡፡ Amh2SM 297.6
አካል ያጣው ጤናማ ተግባር እንዲመለስለት የሚያደርጉ ሌሎች ብዙ ቀላል ፈውሶች አሉ፡፡ እነዚህን ቀላል ዝግጅቶች ለራሳችን እንድንጠቀም እግዚአብሔር ይጠብቅብናል፣ ነገር ግን የሰው አለመቻል እግዚአብሔር ሥራውን የሚሰራበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ እያንዳንዱ ቤተሰብ ማድረግ የሚችለውን ነገር ለማድረግ ችላ ካልን እና በኃይላችን ውስጥ ያሉትን እነዚህን ፈውሶች ለመጠቀም ሰንፈን እግዚአብሔር ሕመምን እንዲያስታግስልን ከጠየቅን ይህ ድፍረት ነው፡፡ እግዚአብሔር ምግብ ለማግኘት እንድንሰራ ይጠብቅብናል፡፡ እዳሪ መሬትን ሳንከሰክስ፣ ሳናርስ እና እህልን ሳንዘራ መከር እንደምንሰበስብ ሀሳብ አይሰጠንም፡፡ እግዚአብሔር ተክሎችን እንዲያሳድግ ዝናብን፣ የፀሐይ ብርሐንን እና ደመናን ይልካል፡፡ ከዚያ በኋላ የዘርና የመከር ጊዜ አለ፡፡ Amh2SM 297.7
እግዚአብሔር እጽዋት ከምድር እንዲበቅሉ ያደረገው ለሰው ጥቅም ስለሆነ የእነዚያን ሥራ ሥሮችና ቅጠላቅጠሎች ባሕርይ ብንረዳ እና በትክክለኛ ሁኔታ ብንጠቀም ኖሮ በየጊዜው ወደ ሐኪም መሄድ አያስፈልግም ነበር፣ ሰዎችም አሁን ካሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም በተሻለ ሁኔታ ጤንነት ይኖራቸው ነበር፡፡ እኔ የጠቀስኳቸውን ፈውሶች በተጠቀምን ጊዜ ታላቁን ሐኪም መጥራት እንዳለብን አምናለሁ፡፡ Letter 35, 1890 (To a worker in overseas field). Amh2SM 297.8