የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

230/349

በተፈጥሮ ዓለም ውስጥ ያሉ ፈውሶች

የውኃ ሕክምና እና ቀላል ቅጠላ ቅጠሎች፡፡ ፈውስን በተመለከተ ትልቅ ውጤት ያለው ውኃን በትክክል በመጠቀም ላይ እንደሆነ ጌታ አስተምሮኛል፡፡ ይህ ሕክምና ጥበብ ባለው ሁኔታ መሰጠት አለበት፡፡ ሕመምተኞችን ስናክም መድሃኒቶችን መጠቀም እንዳለብን መመሪያ ተሰጥቶኛል፡፡ በአካል ላይ የሚያስከትሉት ተጽእኖ ደምን ከሚበክሉና ሕይወትን አደጋ ላይ ከሚጥሉ መድሃኒቶች እጅግ ልዩ ሆነው ሕመምተኞችን ለመፈወስ ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ቀላል ቅጠላ ቅጠሎች አሉ፡፡ Manuscript 73, 1908 (Manuscript entitled “Counsels Repeated”). Amh2SM 288.1

የአካል ክፍሎችን የሚያነጹ ፈውሶች፡፡ ክርስቶስ በአካል ክፍሎች ውስጥ የሞት ዘሮችን በፍጹም አልዘራም፡፡ እነዚህን ዘሮች የዘራው ሰይጣን ሲሆን የዘራውም እግዚአብሔርን ያለመታዘዝ የሆነውን ክፉንና ደግን ከሚያስታውቀው ዛፍ እንዲበላ አዳምን የፈተነው ጊዜ ነበር፡፡ በታላቁ የእግዚአብሔር የአትክልት ቦታ ውሰጥ አንድ መርዘኛ የሆነ ዛፍ አልተቀመጠም ነበር፣ ነገር ግን አዳምና ሔዋን ኃጢአት ከሰሩ በኋላ መርዘኛ የሆኑ ተክሎች በቀሉ፡፡ በዘሪው ምሳሌ ለጌታው እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር፣ «ጌታ ሆይ፣ መልካምን ዘር በእርሻህ ውስጥ ዘርተህ አልነበረምን? እንክርዳዱስ ከወዴት መጣ? አሉት፡፡ እርሱም ጠላት ይህን አደረገ አላቸው» (ማቴ. 13፡ 28፣ 29)፡፡ እንክርዳዶች በሙሉ የተዘሩት በክፉው ነው፡፡ እያንዳንዱ መርዘኛ ተክል እሱ የዘራው ስለሆነ ብልጠት በተሞላ የመደባለቅ ዘዴዎቹ ምድርን በእንክርዳዶች አበላሽቷል፡፡ Amh2SM 288.2

ስለዚህ ሐኪሞች ክርስቶስ ወደ ቀድሞ ሁኔታው ለመመለስ የመጣለትን ሕይወት በማጥፋት በአካል ውስጥ ሞትን የሚያስከትል ክፋትን የሚተዉ መድሃኒቶችን መጠቀማቸውን ይቀጥላሉን? የክርስቶስ ፈውሶች የአካል ክፍሎችን ያነጻሉ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን እግዚአብሔር ጥሩና ውብ አድርጎ ያስቀመጠውን ነገር በመድፈንና በማጥፋት ሰብአዊ ፋብሪካን የሚያዳክሙ ነገሮችን በአካል ውስጥ እንዲጨምር ሰውን ፈትኗል፡፡ ለሕመምተኛ የሚሰጡ መድሃኒቶች ጤንነትን የሚመልሱ ሳይሆኑ የሚያጠፉ ናቸው፡፡ መድሃኒቶች በፍጹም አይፈውሱም፡፡ ከዚያ ይልቅ እጅግ መራራ መከር የሚያፈሩ ዘሮችን በአካል ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡… Amh2SM 288.3

አዳኛችን በሰው ውስጥ የእግዚአብሔርን የግብረገብ ምስል መላሽ ነው፡፡ የእሱ ተከታዮች ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲበዛላቸው በተፈጥሮ ዓለም ውስጥ የሰውን ሕመም የሚፈውሱ ፈውሶችን ሰጥቷል፡፡ ከዚህ በፊት የተጠቀምናቸውን የተቀመሙ መድሃኒቶችን ያለ አንዳች ችግር መተው እንችላለን፡፡ Amh2SM 289.1

እግዚአብሔር በቀላል ተክሎች ውስጥ የበሽታዎችን ማርከሻዎች ስላስቀመጠ እነዚህን ነገሮች እምነትን ሳይክዱ በእምነት መጠቀም ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር ለጥቅማችን የሰጣቸውን በረከቶች ስንጠቀም ከእርሱ ጋር እየተባበርን ነን፡፡ በእንህዝላልነት ወይም በአጋጣሚ የመጡ ሕመሞችን ለመፈወስ ውኃን፣ የፀሐይ ብርሃንን እና ይህ ብርሃን እንዲያድጉ ያደረጋቸውን ተክሎች መጠቀም ይቻላል፡፡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ፈዋሽ ነገሮች እንዲባርክ ስንጠይቅ እምነት ማጣትን አናሳይም፡፡ እውነተኛ እምነት እነዚህን የከበሩ በረከቶች የአእምሮና የአካል ብርታትን በሚመልሱበት መንገድ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ስለ ሰጠው እውቀት እግዚአብሔርን ያመሰግናል፡፡ Amh2SM 289.2

አካል በጥንቃቄ መጠበቅ ያለበት ሲሆን በዚህ ጉዳይ ላይ ሰዎች እንዲተባበሩ ጌታ ይጠይቃል፡፡ የአእምሮን፣ የአጥንትን እና የጡንቻዎችን አያያዝና አጠቃቀም በተመለከተ ሰው ብልህ መሆን አለበት፡፡ ከሁሉ የበለጠ ማግኘት የምንችለው ልምምድ ራሳችንን ማወቅ ነው፡፡ Manuscript 65, 1899 (General Manuscript). Amh2SM 289.3