የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

24/349

ጩኸት የመቀደስ ማስረጃ አይደለም

በኢንዲያና ይካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች በጫጫታና በሁካታ ይካሄዱ የነበሩበት ሁኔታ ተሰብሳቢዎቹ አስተዋይና አሳቢ አእምሮ ያላቸው አያስመስልም ነበር፡፡ በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ እኛ እውነት እንዳለን ዓለምን የሚያሳምን ምንም ነገር የለም፡፡ ዝም ብሎ መንጫጫትና ጩኸት የመቀደስ ወይም የመንፈስ ቅዱስ መውረድ ማስረጃ አይደለም፡፡ የምታሳዩአቸው ሥርዓት የለሽ እንቅስቃሴዎች በማያምኑ ሰዎች ፊት ጥላቻን ብቻ ይፈጥራል፡፡ እንዲህ ዓይነት ነገር የሚያሳዩ ሰዎች ቁጥር ማነስ ለተዋንያኑም ሆነ በአጠቃላይ ለሕዝብ የተሻለ ነገር ነው፡፡ {2SM 35.1} Amh2SM 35.1

ወግ አጥባቂነት አንዴ ከተጀመረና ቁጥጥር ካልተደረገበት በሕንጻ ላይ እንደተያያዘ እሳት ያህል ለማጥፋት ከባድ ነው፡፡ ወደዚህ ወግ አጥባቂነት የገቡና የቆዩበት ሰዎች ተለዋዋጭ በሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን እያዋረዱና ሕዝቡንም በአደጋ ውስጥ እየጣሉ ስለሆነ በዓለማዊ ሥራ ቢሰማሩ ይሻላቸዋል፡፡ የጌታ ሥራ ከፍ ብሎ፣ ከጥንቆላና አፈ ታሪክ ጋር ሳይበከል በንጽህና መቆም ባለበት በዚህ ጊዜ ብዙ የዚህ ዓይነት እንቅስቃሴዎች ይነሳሉ፡፡ በሰይጣን ማታለያዎች እንዳንታለል ከክርስቶስ ጋር ያለንን የቅርብ ግንኙነት ለማቆየት መጠንቀቅ አለብን፡፡ {2SM 35.2} Amh2SM 35.2

እግዚአብሔር በአገልግሎቱ ውስጥ እንዲኖር የሚፈልገው ግርግርና ምስቅልቅል ሳይሆን ጸጥታና ሥርዓት ነው፡፡ ወደ ፊት በዓለማችን ውስጥ ሊሰሩ ያሉ ሁኔታዎችን አሁን በትክክል መግለጽ አንችልም፤ ነገር ግን ታላቁ የጌታ ቀን ቅርብ ስለሆነ አሁን በጸሎት ነቅተን መጠበቅ ያለብን ጊዜ እንደሆነ ይህን እናውቃለን፡፡ ሰይጣን ኃይሎቹን እያሰባሰበ ነው፡፡ አስተዋይና የማንነቃነቅ፣ የራዕይ እውነቶችንም የምናሰላስል መሆን አለብን፡፡ ግርግር በጸጋ ለማደግ፣ ለእውነተኛ ንጽህናና ለመንፈስ ቅድስና አመቺ አይደለም፡፡ {2SM 35.3} Amh2SM 35.3

እግዚአብሔር ቅዱስ እውነትን እንድንንከባከብ ይፈልጋል፡፡ ተቃዋሚን ሊያሳምን የሚችለው ይህ ብቻ ነው፡፡ ነፍሳትን ስላሉበት ሁኔታ ለማሳመን እና ለጌታ ውብ የሆነ የባሕርይ ህንጻ መቆም ካለበት መደረግ ያለበትን የባሕርይ ግንባታ ለማሳየት፣ የተረጋጋ እና ጠቃሚ የሆነ ሥራ መሰራት አለበት፡፡ የተነቃቁ አእምሮዎች የቃሉን እውነቶች በትክክል ካስተዋሉና በሚገባ ካደነቁ በትዕግሥት ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ {2SM 35.4} Amh2SM 35.4

እግዚአብሔር ሕዝቡ በእርጋታና ቅዱስ በሆነ የመንፈስ ጽናት እንዲራመዱ ይጠራቸዋል፡፡ እንግዳ በሆኑ ትርኢቶች፣ ነገሮችን በማመሰቃቀልና ህውከት በመፍጠር ቅዱስ የሆኑ የእውነት አስተምህሮዎችን እንዳያዋርዱና መጥፎ የሆነ ገጽታ እንዳያሰጡ እጅግ መጠንቀቅ አለባቸው፡፡ በዚህ ምክንያት አማኝ ያልሆኑ ሰዎች ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች የጽንፈኞች ስብስብ ናቸው ብለው እንዲያስቡ ተመርተዋል፡፡ ከዚህ የተነሳ ነፍሳት የወቅቱን እውነት እንዳይቀበሉ የሚያደርግ አግባብ የሌለው ጥላቻ ተፈጥሯል፡፡ አማኞች እውነትን ልክ በክርስቶስ እንዳለ ሲናገሩ ግራ የሚያጋባ ወጀብን ሳይሆን ቅዱስ የሆነ፣ ማስተዋል ያለበትን መረጋጋት ያሳያሉ፡፡--General Conference Bulletin, April 23, 1901. {2SM 36.1} Amh2SM 36.1