የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

215/349

ማልቀስ ኃጢአት አይደለም

ባሏ ለሞተባት ባልቴት የተሰጠ ማጽናኛ

ውድ እህት ሆይ፣

በሀዘንሽ እና ባልሽን በማጣትሽ ሀዘንሽን እንጋራለን፡፡ አሁን አንቺ እየሄድሽበት ባለው መንገድ ላይ ስለተጓዝኩ ምን ማለት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ በዓለማችን ውስጥ ያለው ምንኛ ብዙ ሀዘን ነው! እንዴት የበዛ ሀዘን! እንዴት ያለ ብዙ ለቅሶ! በሞት ምክንያት አዝነው ያሉትን ሰዎች “አታልቅሱ፤ ማልቀስ ትክክል አይደለም” ማለት ትክክል አይደለም፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ቃላት አያጽናኑአቸውም፡፡ ማልቀስ ኃጢአት አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሞተው ሰው በድካምና በሕመም ሲሰቃይ የነበረ ቢሆንም ያ ሁኔታ ከዓይኖቻችን እንባችንን አይጠርግልንም፡፡ Amh2SM 264.1

የምንወዳቸው ሰዎች ይሞታሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ጉዳይ ታትሟል፡፡ ሞትን እጅግ አሳሳቢና ከባድ ነገር አድርገን ብናይም በሕይወት መኖርን ከዚያ የበለጠ ከባድ ነገር አድርገን ማየት ያስፈልጋል፡፡ የእያንዳንዱ ቀን ሕይወት መሸከም ባለብን ሀላፊነቶች የተጫነ ነው፡፡ የግል ፍላጎቶቻችን፣ ቃሎቻችን፣ ተግባሮቻችን፣ ከእኛ ጋር ግንኙነት ባላቸው ላይ አሻራ እያሳረፉ ናቸው፡፡ ማጽናኛ ማግኘት ያለብን በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክቡር አዳኝ! ሰብአዊ ዋይታ ነክቶታል፡፡…የብርታትሽ ምንጭ በሆነው ላይ ተጣበቂ፡፡…Letter 103, 1898. Amh2SM 264.2