የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

213/349

ትኩረትን አስደሳች ወደሆነው የቤተሰብ እንደገና መገናኘት ማዞር

ሚስቱ ለሞተችበት ሰው የተሰጠ ማጽናኛ

ውድ ወንድም ሆይ፣

የባለቤትህን ሞት ወሬ ሰምተናል፣ ነገር ግን ስለ ሕመሟ ምንም የሰማነው ነገር አልነበረም፡፡ Amh2SM 262.1

ሃዘንህን እንጋራለን፡፡ ከመጠን ባለፈ ሀዘን እንዳትደክም ጌታ እንዲያጽናናህና ፀጋውን እንዲሰጥህ እንጸልያለን፡፡ ፊታችን ቃል ወደተገባልን ውርስ ስለዞረ እግዚአብሔርን እናመስግን፡፡ ማዳኑ ሩቅ ሳይሆን ቅርብ ስለሆነ እርሱን እናመስግነው፡፡ Amh2SM 262.2

ባለቤትህ በሕይወት ሳለች የእናትነት ሀላፊነቷን በታማኝነት ስትወጣ ለነበሩአዋቸው ሕጻናት ስትጠነቀቅ ሳለ እነዚህን ልጆች በእግዚአብሔር ተግሳጽ ለማሳደግ ማድረግ የምትችለውን ሁሉ ስላደረገች ደስ ይበልህ፡፡ ሕጻናትን በክንዶቹ ተሸክሞ የባረካቸው የተባረከው አዳኝ ልጆችህንም ሆነ አንተን ያለመጽናኛ አይተውም፡፡ አሁን ድርብ ሀላፊነት ያርፍብሃል፡፡ በክርስቶስ በረት ውስጥ ላሉ ለእነዚህ ጠቦቶች የሚጠነቀቁ ሰዎች እነዚህን ለጋና ልምድ የሌላቸውን እግሮች ከአደጋ ነጻ በሆነ ሁኔታ መሄድ እንዲችሉ ለመምራት በጨዋነት፣ በገርነት እና በፍቅር መያዝ እንዲችሉ ጌታ ልባቸውን ያነሳሳ፡፡ Amh2SM 262.3

ውድ ሕጻናት ሆይ፣ እህት ኋይት ትወዳችኋለች፣ አዳኙ እንደ ትንንሽ ልጆቹ አድርጎ ስለሚመለከታችሁ እንዲባርካችሁ ትጸልይላችኋለች፡፡ Amh2SM 262.4

ወንድም ኢ ሆይ፣ ለልብህ ውድ የሆነችውን ስለቀበርክ እንደምታዝን አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ምን ይላል? Amh2SM 262.5

“የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው፡፡ ከሰማይ፡- ከእንግዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብጹአን ናቸው፡፡ መንፈስ፡- አዎን፣ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፣ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምጽ ሰማሁ” (ራዕይ 14፡ 12፣ 13)፡፡ Amh2SM 262.6

መልካምን በማድረግ በትዕግሥት ወደፊት በመቀጠል ፊታችሁና እርምጃችሁ ሁልጊዜ ወደ ላይ እንዲያቀና ለአንተና ውድ ለሆኑት ልጆችህ እንጸልያለን፡፡ እነዚህን ትንንሽ ልጆች በመምራት ተጽዕኖ ማሳደር እንድትችልና ስኬታማ እንድትሆን፣ አንተም ከእነርሱ ጋር አብረህ የሕይወት አክሊልን እንድታገኝ፣ አሁን ለእኛ እየተዘጋጀ ባለው በላይኛው ቤት አንተ፣ ባለቤትህና ልጆችህ በፍጹም ላትለያዩ በደስታና በፍስሃ ለመኖር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንድትፈጥሩ እንጸልይላችኋለን፡፡ Amh2SM 262.7

በብዙ ፍቅርና ፍህራሄ፡፡--Letter 143, 1903. Amh2SM 263.1