የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

20/349

የስራውን ቅድስና ማጉደፍ

በወንጌል አገልጋዮች እና የእውነትን ብርሃን ለዓለም እየሰጡ እንደሆነ በሚናገሩ ሰዎች ፊት ሥራው እንዲሰራ እግዚአብሔር ስለሚፈልግበት መንገድ ከሚሰጠው ርካሽ ትርጉም ጋር አእምሮ እንዲስማማ በመፍቀድ የእግዚአብሔርን ቅድስና የማጉደፍ አደጋ እንዳለ በሕዝባችን ፊት ሁል ጊዜ እንዳስቀምጥ ታዝዣለሁ፡፡ የወቅቱን እውነት ለዓለም በማሳወቅ ሥራ ውስጥ ሰብዓዊ እቅዶችንና ዘዴዎችን ማምጣትን በተመለከተ ልዩ መመሪያ ተሰጥቶኝ ነበር፡፡ {2SM 28.1} Amh2SM 28.1

ባለፉት አመታት በአንድ ወይም በሌላ ሰው ሲቀርቡ የነበሩትን ብልጭልጭና የተከለከሉ ዘዴዎች በመቃወም እንድናገር ታዝዤ ነበር፡፡ ሁል ጊዜ መልእክቴ የነበረው ቃሉን በትህትናና ራስን ዝቅ በማድረግ ስበኩ፣ ግልጽና ያልተበከለ እውነትን ለሕዝብ ስጡ፡፡ የወግ አጥባቂነት እንቅስቃሴዎች ተጽእኖ የአእምሮ ግራ መጋባትንና ተስፋ መቁረጥን፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ሕዝብ የእምነት እጦትን ማምጣት ስለሆነ ለእነዚህ እንቅስቃሴዎች ምንም በር አትክፈቱ የሚል ነበር፡፡ . . . {2SM 28.2} Amh2SM 28.2

ወግ አጥባቂነትን በተለያየ መልኩ ለመጋፈጥ በተጠራሁበት ጊዜ ሁሉ ተጽእኖውን በመቃወም ድምጼን ከፍ እንዳደርግ ግልጽ፣ አዎንታዊና የማያወላውል መመሪያ ተቀብያለሁ፡፡ በአንዳንዶች ዘንድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እውቀት ለማረጋገጥ ሰው ሰራሽ መፈተኛዎችን በማስቀመጥ ክፉው ራሱን ገልጧል፡፡ ይህ አእምሮን የሚያስት ፍቅር ወደ መሆን ደረጃ የደረሰ ማታለያ እንደሆነና የእግዚአብሔር ፈቃድ ተቃራኒ እንደሆነ እንዳይ ተደረግሁ፡፡ እነዚህን ዘዴዎች ከተከተልን የጠላትን እቅዶች በመደገፍ ላይ እንገኛለን፡፡ ባለፉት ዘመናት ከአማኞች መካከል አንዳንዶች ሥራቸውን ለመወሰን ምልክቶችን በማስቀመጥ ላይ ታላቅ እምነት ነበራቸው፡፡ አንዳንዶች በእነዚህ ምልክቶች ላይ ትልቅ እምነት ከማስቀመጣቸው የተነሳ ወንዶች ሚስቶቻቸውን እስከመቀያየር ደረጃ በመድረስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ዝሙትን አምጥተዋል፡፡ {2SM 28.3} Amh2SM 28.3

በመልእክታችን ቀደምት ልምምድ ወቅት እንድንጋፈጣቸው ተጠርተን የነበረው ዓይነት ማታለያዎች እንደሚደገሙና ሥራው በሚዘጋበት ወቅትም እንደገና እንደምንጋፈጣቸው እንዳይ ተደርጌ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ኃይሎቻችንን በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር እንድናመጣና የአካል ክፍሎቻችንን እርሱ በሰጠን ብርሃን መሠረት በሥራ ላይ እንድናውላቸው ይጠበቅብናል፡፡ የማቴዎሰ ወንጌል 4ኛውንና 5ኛውን ምዕራፎች አንብቡ፡፡ ማቴዎች 4፡ 8-10ን እና 5፡ 13ን አጥኑ፡፡ ክርስቶስ የሰራውን ቅዱስ ሥራ አሰላስሉ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል መርሆዎች በሥራዎቻችን ውስጥ መምጣት ያለባቸው እንዲህ ባለ ሁኔታ ነው፡፡ --Letter 36, 1911. {2SM 28.4} Amh2SM 28.4